From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ አይደለህም ፡ ሰዎች ፡ እንደሚሉት
አይደለህም ፡ ብዙዎች ፡ እንደሚናገሩት
አይደለህም ፡ ሁኔታ ፡ እንደሚያወራው
አይደለህም ፡ ሰነፍ ፡ እንደሚናገረው
አምላኬ ፡ ቃልህ ፡ እንደሚልህ ፡ ነህ
እንደሚልህ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ቃልህ
ጌታዬ ፡ ቃልህ ፡ እንደሚልህ ፡ ነህ
እንደሚልህ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ቃልህ
እረሳሀን ፡ ተውከን ፡ ሲሉ ፡ ብዙዎች ፡ እሰማለው
በምድር ፡ ላይ ፡ ሕይወት ፡ ብርቱ ፡ሰልፍ ፡ ሆኖባቸው
እኔ ፡ ግን ፡ አንተን ፡ ሳይ ፡ ተራራው ፡ ይከለልብኛል
ዘንድሮ ፡ ሰዎች ፡ ከሚሉህ ፡ ለእኔ ፡ ተለይተሃል (፪x)
አዝ፦ አይደለህም ፡ ሰዎች ፡ እንደሚሉት
አይደለህም ፡ ብዙዎች ፡ እንደሚናገሩት
አይደለህም ፡ ሁኔታ ፡ እንደሚያወራው
አይደለህም ፡ ሰነፍ ፡ እንደሚናገረው
አምላኬ ፡ ቃልህ ፡ እንደሚልህ ፡ ነህ
እንደሚልህ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ቃልህ
ጌታዬ ፡ ቃልህ ፡ እንደሚልህ ፡ ነህ
እንደሚልህ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ቃልህ
ደመና ፡ ባይጠቁር ፡ ነፋስ ፡ ባይነፍስም
የአየሩ ፡ ሁኔታ ፡ ህልውህን ፡ ባይገልጥህ
እኔ ፡ ግን ፡ አንተን ፡ ሳይ ፡ ሸለቆው ፡ ይሞላልኛል
ዘንድሮ ፡ ሰዎች ፡ ከሚያዩህ ፡ ለእኔ ፡ ተለይተሃል (፪x)
አዝ፦ አይደለህም ፡ ሰዎች ፡ እንደሚሉት
አይደለህም ፡ ብዙዎች ፡ እንደሚናገሩት
አይደለህም ፡ ሁኔታ ፡ እንደሚያወራው
አይደለህም ፡ ሰነፍ ፡ እንደሚናገረው
አምላኬ ፡ ቃልህ ፡ እንደሚልህ ፡ ነህ
እንደሚልህ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ቃልህ
ጌታዬ ፡ ቃልህ ፡ እንደሚልህ ፡ ነህ
እንደሚልህ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ቃልህ
አምላኬ ፡ ቃልህ ፡ እንደሚልህ ፡ ነህ
እንደሚልህ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ቃልህ
ጌታዬ ፡ ቃልህ ፡ እንደሚልህ ፡ ነህ
እንደሚልህ ፡ ነህ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ቃልህ (፪x)
|