ታስገርማለህ (Tasgeremaleh) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 1.jpg


(1)

የሚገርመኝ ፡ መዳኔ ፡ ነው
(Yemigermegn Medanie New)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

አዝ፦ ታስገርማለህ ፡ እኔም ፡ ተገርሜያለሁ
ታስደንቃለህ ፡ በልቤ ፡ ተደንቄያለሁ
ታስደስታለህ ፡ እኔም ፡ ተደስቻለሁ
ታስፈነድቃለህ ፡ በልቤ ፡ ፈንድቄያለሁ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ አክብሮት ፡ ሲያንስህ ፡ ነው (፪x)

ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ
ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ኢየሱስ
ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ
ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ኢየሱስ
አድርገህልኛልና ፡ ለዘለዓለም ፡ አመሰግንሃለሁ
ለዘለዓለም ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)

ፈረሱን ፡ ፈረሰኛውን ፡ በባሕር ፡ ጥለህልኛል
አቅም ፡ ያጣሁትን ፡ ክንድህ ፡ አሻግሮኛል
ከወጀቡ ፡ ወዲያ ፡ ቆሜ ፡ በድል ፡ እዘምራለሁ
ጉልበቴም ፡ ዝማሬዬም ፡ ሆነህልኝ ፡ ስላየሁ

አዝ፦ ታስገርማለህ ፡ እኔም ፡ ተገርሜያለሁ
ታስደንቃለህ ፡ በልቤ ፡ ተደንቄያለሁ
ታስደስታለህ ፡ እኔም ፡ ተደስቻለሁ
ታስፈነድቃለህ ፡ በልቤ ፡ ፈንድቄያለሁ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ አክብሮት ፡ ሲያንስህ ፡ ነው (፪x)

ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ
ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ኢየሱስ
ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ
ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ኢየሱስ
አድርገህልኛልና ፡ ለዘለዓለም ፡ አመሰግንሃለሁ
ለዘለዓለም ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)

በእሳት ፡ በዳመና ፡ ተገልጠህ ፡ ጠላቴን ፡ ተመለከትከው
ወደ ፡ ጭንቅ፡ አገባህና ፡ መዳኔን ፡ አፈጠንከው
እንደምትዋጋልኝ ፡ አይተው ፡ ሊሸሹ ፡ ሲማከሩ
ውሃው ፡ ጠላት ፡ ሆነባቸው ፡ ተከደነ ፡ ባሕሩ

አዝ፦ ታስገርማለህ ፡ እኔም ፡ ተገርሜያለሁ
ታስደንቃለህ ፡ በልቤ ፡ ተደንቄያለሁ
ታስደስታለህ ፡ እኔም ፡ ተደስቻለሁ
ታስፈነድቃለህ ፡ በልቤ ፡ ፈንድቄያለሁ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው
የእኔ ፡ ጌታ ፡ አክብሮት ፡ ሲያንስህ ፡ ነው (፪x)

ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ
ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ኢየሱስ
ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ
ባከብርህ ፡ ይገባሃል ፡ ኢየሱስ
አድርገህልኛልና ፡ ለዘለዓለም ፡ አመሰግንሃለሁ
ለዘለዓለም ፡ አመሰግንሃለሁ (፪x)