ስላንተ (Selante) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 1.jpg


(1)

የሚገርመኝ ፡ መዳኔ ፡ ነው
(Yemigermegn Medanie New)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

አዝ፦ ስለአንተ ፡ ብዘምር ፡ ልገልጽህ ፡ ብሞክር
ቃላት ፡ ብደረድር ፡ ባበዛ ፡ ብደምር
አይገልጽህም ፡ አንተን ፡ አሃሃሃ
አይገልጽህም ፡ አንተን (፪x)
ስለአንተ ፡ ብዘምር ፡ ልገልጽህ ፡ ብሞክር
ቃላት ፡ ብደረድር ፡ ባበዛ ፡ ብደምር
አይበቃህም ፡ ለአንተ ፡ አሃሃሃ
አይበቃህም ፡ ለአንተ (፪x)

አንደበት ፡ ያለው ፡ ቢዘምር ፡ ቢፈቀድለት ፡ ሊያወራ
መቼ ፡ ተተርኮ ፡ ያልቃል ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ስራ
እስትንፋስ ፡ ያለው ፡ ቢደክም ፡ ግዑዙም ፡ ተራ ፡ ቢደርሰው
ጥበብህ ፡ ቁጥር ፡ የለውም ፡ ከተነገረው ፡ በላይ ፡ ነው

አዝ፦ ስለአንተ ፡ ብዘምር ፡ ልገልጽህ ፡ ብሞክር
ቃላት ፡ ብደረድር ፡ ባበዛ ፡ ብደምር
አይገልጽህም ፡ አንተን ፡ አሃሃሃ
አይገልጽህም ፡ አንተን (፪x)
ስለአንተ ፡ ብዘምር ፡ ልገልጽህ ፡ ብሞክር
ቃላት ፡ ብደረድር ፡ ባበዛ ፡ ብደምር
አይበቃህም ፡ ለአንተ ፡ አሃሃሃ
አይበቃህም ፡ ለአንተ (፪x)

መላዕክት ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቢሉም ፡ ሌሊትና ፡ ቀን
በሰማያዊ ፡ ቋንቋ ፡ ና ፡ ዜማ ፡ ብትመሰገን
ከሁሉ ፡ በፊት ፡ የነበርክ ፡ ዘመንህ ፡ አልተቆጠረም
ስለዚህ ፡ ዕድሜህን ፡ ያህን ፡ ተችሎት ፡ ማን ፡ ተናገረ

አዝ፦ ስለአንተ ፡ ብዘምር ፡ ልገልጽህ ፡ ብሞክር
ቃላት ፡ ብደረድር ፡ ባበዛ ፡ ብደምር
አይገልጽህም ፡ አንተን ፡ አሃሃሃ
አይገልጽህም ፡ አንተን (፪x)
ስለአንተ ፡ ብዘምር ፡ ልገልጽህ ፡ ብሞክር
ቃላት ፡ ብደረድር ፡ ባበዛ ፡ ብደምር
አይበቃህም ፡ ለአንተ ፡ አሃሃሃ
አይበቃህም ፡ ለአንተ (፪x)