From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አቤኔዘር ፡ አቤኔዘር ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን
አቤኔዘር ፡ አቤኔዘር ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን
እስካሁን ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን
እስካሁን ፡ እግዚአብሔር ፡ እረዳን (፪x)
እኛም ፡ ደግሞ ፡ የረዳንን
ልዑል ፡ እግዚአብሔርን ፡ እናመልካለን
. (1) . ፡ ኮረብቶች ፡ ወንዞችን ፡ አፈሰሱ
በሸለቆችም ፡ መካከል ፡ ምንጮች ፡ ተከፈቱ
ምድረበዳው ፡ ረሰረሰ ፡ ከጥማት ፡ ምድር ፡ ውኃ ፡ ፈለቀ
እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ የእኛን ፡ ጩኸት ፡ አደመጠ
በእኛ ፡ ላይ ፡ ታወቀ
አዝ፦ አቤኔዘር ፡ አቤኔዘር ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን
አቤኔዘር ፡ አቤኔዘር ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን
ብቻውን ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን
ብቻውን ፡ እግዚአብሔር ፡ እረዳን (፪x)
እኛም ፡ ደግሞ ፡ የረዳንን
ልዑል ፡ እግዚአብሔርን ፡ እናመልካለን
ወጥመድ ፡ ቢዘረጋ ፡ አሃሃሃሃ ፡ ጉድጓድም ፡ ቢቆፍር
ጠላቴ ፡ ሊይዘኝ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ቢሞክር
ቢመስለኝም ፡ ምወድቅ ፡ ፈጽሞ ፡ ምጠፋ
ጌታዬ ፡ ሆኖኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ አሜን
ስለዚህ ፡ አለሁ ፡ አልጠፋሁም
ሸንበቆን ፡ አልተደገፍኩም
ይረዳኛል ፡ ኃይሌ ፡ ነው
በአምላኬ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ (፪x)
አምላክ ፡ ነህና ፡ አምላክ ፡ ነህና (፪x)
ላምልክህ ፡ እንደገና (፬x)
አምላክ ፡ ነህና ፡ ላምልክህ ፡ እንደገና
አምላክ ፡ ነህና ፡ ላምልክህ ፡ እንደገና
አንዳንዶች ፡ የሰይጣን ፡ ቀንበሩ ፡ ከብዷቸው
ጅማሬ ፡ ላይ ፡ ቀሩ ፡ ጠፍቶ ፡ ሚረዳቸው
ሲያገለግሉ ፡ ሰይጣንን ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ሲሉ
ተሰብሮ ፡ ወጋቸው ፡ ምርኩዙ ፡ ጠፍተው ፡ በዚያው ፡ ቀሩ
እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ አልጠፋሁም
ቀንበር ፡ ከብዶኝ ፡ አልጐበጥኩም
ቀና ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ
በአምላኬ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ
በፀጋሁ ፡ አለሁ ፡ አልጠፋሁም
ቀንበር ፡ ከብዶኝ ፡ አልጐበጥኩም
ቀና ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ
በአምላኬ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አምላክ ፡ ማነው?
ሌላ ፡ አምላክ ፡ ማነው? (፪x)
ሳስብህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
ኩራትም ፡ ይሰማኛል
ከልቤ ፡ ደስታ ፡ ፈንቅሎ
አዘለለኝ ፡ ወጣሁ ፡ ከእሮሮ (፭x)
|