ልመናዬ (Lemenayie) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 1.jpg


(1)

የሚገርመኝ ፡ መዳኔ ፡ ነው
(Yemigermegn Medanie New)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

የተማረውን ፡ ሕይወት ፡ አንተን ፡ የሚያሳየው
እንድትሰጠኝ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ልመናዬ ፡ ነው
የተማረውን ፡ ምላስ ፡ አንተን ፡ የሚያከብረው
እንድትሰጠኝ ፡ ጌታ ፡ ሁልጊዜ ፡ ልመናዬ ፡ ነው

ልመናዬ ፡ ሌላ ፡ አይደለም ፡ ኦሆሆሆ
ልመናዬ ፡ ሌላ ፡ አይደለም ፡ ኦሆሆሆ
ልመናዬ ፡ ሌላ ፡ አይደለም ፡ ኦህህህ
ልመናዬ ፡ ሌላ ፡ አይደለም

በዚህ ፡ ጉብዝናዬ (፪x)
በዚህ ፡ ወጣትነት (፪x)
አንተው ፡ ታይበት (፪x)
ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እሻለሁ (፪x)
ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ ምን ፡ እሻለሁ
ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እሻለሁ

በዚህ ፡ ጉብዝናዬ (፪x)
በዚህ ፡ ወጣትነት (፪x)
ፍቅርህ ፡ ማረከኝ (፪x)
ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እሻለሁ (፪x)
ከአንተ ፡ ወዲያ ፡ ምን ፡ እሻለሁ (፪x)

ስለፍቅር ፡ ቢወራ ፡ ባለሁበት
ምናገረው ፡ አለኝ ፡ የቀመስኩት
ለውድድር ፡ የማይቀርብ ፡ የማይመች
ነፍሴን ፡ ደግሞ ፡ ለራሱ ፡ የማረካት
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ እኔ ፡ አላየሁም (፪x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ እኔ ፡ አልሰማሁም (፪x)

ስለፍቅር ፡ ቢወራ ፡ ባለሁበት
ምናገረው ፡ አለኝ ፡ የቀመስኩት
ለውድድር ፡ የማይቀርብ ፡ የማይመች
ነፍሴን ፡ ደግሞ ፡ ለራሱ ፡ የማረካት
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ እኔ ፡ አላየሁም (፪x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ እኔ ፡ አልሰማሁም (፪x)