From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ምህረትህ ፡ ጌታዬ ፡ ምህረትህ
ምህረትህ ፡ አምላኬ ፡ ምህረትህ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ነው
ለዚህ ፡ መድረሴ (፬x)
ምህረትህ ፡ እንዴት ፡ በዝቷል
ከፍ ፡ ብሏል ፡ ለእኔስ ፡ ገኗል (፪x)
በበደሉ ፡ ምክንያት ፡ ጠፍቶ ፡ የነበረው ፡ ሰው
ከጥፋት ፡ ጐዳና ፡ በፍቅርህ ፡ መለስከው
የክህነቱን ፡ ስራ ፡ ኑሮው ፡ አድርጐታል
ያዳነውን ፡ አምላኩን ፡ ሁሌ ፡ ይቀድሰዋል (፪x)
ምህረትህ (፬x) ፡ ለእኔ ፡ በዝቷል
ምህረትህ (፬x) ፡ ለእኔ ፡ በዝቷል
ብብዙዎችም ፡ መካከል (አመሰግንሃለሁ)
ቸርነትህ ፡ ምድርን ፡ ሞልቷል (እዘምረዋለሁ)
የስምህ ፡ ትርጉም ፡ ገብቶኛል (ሁሌ ፡ እጠራዋለሁ)
ብብዙዎችም ፡ መካከል (አመሰግንሃለሁ)
ቸርነትህ ፡ ምድርን ፡ ሞልቷል (እዘምረዋለሁ)
ኢየሱስ ፡ ማለት ፡ ገብቶኛል (ሁሌ ፡ እጠራዋለሁ)
ንጉሥ ፡ ንጉሥን ፡ ሲሽረው
ኃያል ፡ ኃያሉን ፡ ሲያወርደው
ጊዜው/አንዱ ፡ ሲያልፍ ፡ ሲተካ ፡ በሌላ ፡ ጌታ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ሁሌ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ (፪x)
አይቼዋለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ እኔም ፡ በኑሮዬ ፡ አሃሃ
አመታት ፡ ኤለፉ ፡ አላለፈም ፡ ጌታዬ
አይቼዋለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ እኔም ፡ በኑሮዬ ፡ አሃሃ
ዘመናት ፡ አለፉ ፡ አላለፈም ፡ ጌታዬ
አይቼዋለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ እኔም ፡ በኑሮዬ ፡ አሃሃ
ኃያላን ፡ አለፉ ፡ አላለፈም ፡ ጌታዬ
አይቼዋለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ እኔም ፡ በኑሮዬ ፡ አሃሃ
ብዙዎች ፡ አለፉ ፡ አላለፈም ፡ ጌታዬ
ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
አመልከዋለሁ ፡ ይህን ፡ ጌታ (፪x)
ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ሾመዋለሁ ፡ በከፍታ (፪x)
ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
አስበዋለሁ ፡ በመኝታ (፪x)
ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
እደነቃለሁ ፡ በዚህ ፡ ጌታ (፪x)
|