ከፍ ፡ በል (Kef Bel) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 1.jpg


(1)

የሚገርመኝ ፡ መዳኔ ፡ ነው
(Yemigermegn Medanie New)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

በዚያ ፡ በክፉ ፡ ቀን ፡ በጨለማ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ጩኸቴን ፡ ሰማ (፪x)
ደጃፌን ፡ ዘግቼ ፡ ያኔ ፡ የነገርኩህ (፪x)
ያን ፡ ቀን ፡ ታስቦልኝ ፡ በእርሱ ፡ በዓይኔ ፡ አየሁህ (፪x)

አቤት ፡ ጌታዬ ፡ ምስኪኑን ፡ ሲረዳ
አቤት ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲደርስ ፡ ለተጐዳ
አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ምስኪኑን ፡ ሲረዳ
አየሁ ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲደርስ ፡ ለተጐዳ

እርሱንማ ፡ በእውነት ፡ ለሚጠሩ
የቅርብ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ የሩቅ
ጌታንማ ፡ በእምነት ፡ ለሚጠሩ
የቅርብ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ የሩቅ (፪x)

ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)
እርካታዬ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x)
ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)
ተድላዬ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x)

በጉባኤ ፡ መሃል ፡ ስትከብር ፡ እያየሁ
እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ
ሕዝብህ ፡ ሲያደንቅህ ፡ እያየሁ
እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ
አምሮብህ ፡ ተውበህ ፡ እያየሁ
እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ

ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)
ሹመቴ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x)
ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)
ድምቀቴ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x)

ችግረኛ ፡ ሲጮህ ፡ ሰምተህ ፡ ዝም ፡ አትልም (፪x)
የምስኪኑን ፡ ውድቀት ፡ አይተህ ፡ እንዳላየህ ፡ አትሆንም (፪x)
እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ ሁሉን ፡ ትረዳለህ (፪x)
አደራረግህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x)

አቤት ፡ ጌታዬ ፡ ምስኪኑን ፡ ሲረዳ
አቤት ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲደርስ ፡ ለተጐዳ
አየሁ ፡ ጌታዬን ፡ ምስኪኑን ፡ ሲረዳ
አየሁ ፡ ኢየሱሴ ፡ ሲደርስ ፡ ለተጐዳ

እርሱንማ ፡ በእውነት ፡ ለሚጠሩ
የቅርብ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ የሩቅ
ጌታንማ ፡ በእምነት ፡ ለሚጠሩ
የቅርብ ፡ እንጂ ፡ አይደለም ፡ የሩቅ (፪x)

ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)
እርካታዬ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x)
ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)
ተድላዬ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x)

መቃብር ፡ ተከፍቶ ፡ እያየሁ
እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ
ድንጋይ ፡ ተንከባሎ ፡ እያየሁ
እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ
ዲያቢሎስ ፡ ሲረገጥ ፡ እያየሁ
እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ እላለሁ ፡ እንዴት ፡ ችላለሁ

ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)
ሹመቴ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x)
ከፍ ፡ በል ፡ ከሁሉ ፡ በላይ (፪x)
ድንቀቴ ፡ ስትከብር ፡ ሳይ (፪x)