ክብር ፡ ይሁን (Keber Yehun) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 1.jpg


(1)

የሚገርመኝ ፡ መዳኔ ፡ ነው
(Yemigermegn Medanie New)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ብዙ ፡ ጌቶች ፡ ገዝተውን ፡ ነበር
እኛስ ፡ አላየንም ፡ እንደአንተ ፡ የሚሆን
እጅግ ፡ ወደንሃል ፡ ለዘለዓለም ፡ ግዛን (፪x)

ክብር ፡ ይሁን ፡ ከክብርም ፡ በላይ
ሞገስ ፡ ከሞገሥም ፡ በላይ
ጌታ ፡ ነህና ፡ ኤልሻዳይ (፪x)

ሃሳብህ ፡ የሰላም ፡ ነው ፡ ሁልጊዜ ፡ ለሕዝብህ
አላማህ ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ለልጆችህ
የልብህ ፡ እርካታ ፡ ሰዎችን ፡ ማዳን ፡ ነው
በቤትህ ፡ መኖር ፡ ጌታ ፡ ሕይወትን ፡ ማትረፍ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ብዙ ፡ ጌቶች ፡ ገዝተውን ፡ ነበር
እኛስ ፡ አላየንም ፡ እንደአንተ ፡ የሚሆን
እጅግ ፡ ወደንሃል ፡ ለዘለዓለም ፡ ግዛን (፪x)

ክብር ፡ ይሁን ፡ ከክብርም ፡ በላይ
ሞገስ ፡ ከሞገሥም ፡ በላይ
ጌታ ፡ ነህና ፡ ኤልሻዳይ (፪x)

ለጥያቄዎች ፡ ሁሉ ፡ በቤትህ ፡ መልስ ፡ አለ
ለሁሉም ፡ እንደአመሉ ፡ ትናገረዋለህ
ወደ ፡ አንተ ፡ የመጣ ፡ ማነው ፡ ሳያርፍ ፡ የሄደ
ቤትህን ፡ ወደድነው ፡ ጌታ/ኢየሱስ ፡ ለሁሉም ፡ ዕረፍት ፡ አለ (፪x)

አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ብዙ ፡ ጌቶች ፡ ገዝተውን ፡ ነበር
እኛስ ፡ አላየንም ፡ እንደአንተ ፡ የሚሆን
እጅግ ፡ ወደንሃል ፡ ለዘለዓለም ፡ ግዛን (፪x)

ክብር ፡ ይሁን ፡ ከክብርም ፡ በላይ
ሞገስ ፡ ከሞገሥም ፡ በላይ
ጌታ ፡ ነህና ፡ ኤልሻዳይ (፪x)

ለእርስትህ ፡ የምትራራ ፡ ሕዝብህን ፡ ምታከብር
ለጠላት ፡ መላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትሰጥም
እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ መልካም ፡ ትሁት ፡ እረኛ
በሕይወት ፡ ዘመናችን ፡ ኢየሱስ ፡ አላየንም ፡ እኛ (፪x)

አዝ፦ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ብዙ
ብዙ ፡ ጌቶች ፡ ገዝተውን ፡ ነበር
እኛስ ፡ አላየንም ፡ እንደአንተ ፡ የሚሆን
እጅግ ፡ ወደንሃል ፡ ለዘለዓለም ፡ ግዛን (፪x)

ክብር ፡ ይሁን ፡ ከክብርም ፡ በላይ
ሞገስ ፡ ከሞገሥም ፡ በላይ
ጌታ ፡ ነህና ፡ ኤልሻዳይ (፪x)