ኢየሱስ ፡ ሥራህ (Eyesus Serah) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 1.jpg


(1)

የሚገርመኝ ፡ መዳኔ ፡ ነው
(Yemigermegn Medanie New)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 8:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

አዝ፦ አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው (፪x)

የወደቀን ፡ ማንሳት ፡ ስራህ ፡ ነው (፪x)
ማብቃት ፡ ለሽልማት ፡ ስራህ ፡ ነው (፪x)
የታሰረን ፡ መፍታት ፡ ስራህ ፡ ነው (፪x)
ፈቶም ፡ ነጻ ፡ ማውጣት ፡ ስራህ ፡ ነው (፪x)

እኔ ፡ ግን ፡ የሚገርመኝ
ሁልጊዜ ፡ የሚደንቀኝ
መዳኔ ፡ ነው ፡ መትረፌ ፡ ነው
ከሲዖል ፡ ማምለጤ ፡ ነው

እኔ ፡ ግን ፡ የሚገርመኝ
ሁልጊዜ ፡ የሚደንቀኝ
መዳኔ ፡ ነው ፡ መትረፌ ፡ ነው
ልጅህ ፡ መባሌ ፡ ነው

አዝ፦ አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው (፪x)

ባሕርን ፡ ማሻገር ፡ ስራህ ፡ ነው (፪x)
ፈርዖንን ፡ ማስጣል ፡ ስራህ ፡ ነው (፪x)
ማኖር ፡ በበረሃ ፡ ስራህ ፡ ነው (፪x)
እያፈለቅህ ፡ ውሃ ፡ ስራህ ፡ ነው (፪x)

እኔ ፡ ግን ፡ የሚገርመኝ
ሁልጊዜ ፡ የሚደንቀኝ
መዳኔ ፡ ነው ፡ መትረፌ ፡ ነው
ከሲዖል ፡ ማምለጤ ፡ ነው

እኔ ፡ ግን ፡ የሚገርመኝ
ሁልጊዜ ፡ የሚደንቀኝ
መዳኔ ፡ ነው ፡ መትረፌ ፡ ነው
ልጅህ ፡ መባሌ ፡ ነው

አዝ፦ አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
አቤቱ ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው (፪x)

ከሰማይ ፡ መውረድህ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪x)
ደምህን ፡ ማፍሰስህ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪x)
መስቀል ፡ ላይ ፡ መሞትህ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪x)
ደግሞ ፡ መነሳትህ ፡ ለእኔ ፡ ነው (፪x)

ይህን ፡ ሳይ ፡ የሚገርመኝ
ሁልጊዜ ፡ የሚደንቀኝ
መዳኔ ፡ ነው ፡ መትረፌ ፡ ነው
ከሲዖል ፡ ማምለጤ ፡ ነው

ይህን ፡ ሳይ ፡ የሚገርመኝ
ሁልጊዜ ፡ የሚደንቀኝ
መዳኔ ፡ ነው ፡ መትረፌ ፡ ነው
ልጅህ ፡ መባሌ ፡ ነው

እኔ ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ለሰዎች ፡ ባወራ
ገልጬ ፡ ማሳየው ፡ ዘርዝሬ ፡ በተራ
እኔ ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ ለሰዎች ፡ ባወራ
ገልጬ ፡ ማሳየው ፡ ቆጥሬ ፡ በተራ
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ የለኝም
ሌላ ፡ ነገር ፡ የለኝም
ከአንተ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ ነገር ፡ የለኝም
ሌላ ፡ ነገር ፡ የለኝም (፪x)