እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም (Endante Yale Yelem) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 1.jpg


(1)

የሚገርመኝ ፡ መዳኔ ፡ ነው
(Yemigermegn Medanie New)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:52
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ስለሰራኸው ፡ ስራ ፡ ስላደረከው ፡ ነገር
ስለሰራኸው ፡ መዳን ፡ ስላደረከው ፡ ተዓምር
ምን ፡ እንከፍልሃለን ፡ ተመስገን (፬x)

እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፪x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ እላለሁ (፪x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም (፪x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ እላለሁ (፪x)

አዝ፦ ብርሃንህን ፡ በልቤ ፡ አብርተህልኛል
ጨለማዬን ፡ ሁሉ ፡ ገፈህልኛል
አቤቱ ፡ ከልቤ ፡ ላመስግንህ(፪x)
ኢየሱስ ፡ ከልቤ ፡ ላመስግንህ(፪x)

በእኔ ፡ ላይ ፡ እንዳይሰለጥን ፡ የቀድሞው ፡ ጨለማ
የዋይቶ ፡ የለቅሶ ፡ ድምጽ ፡ ከእንግዲህ ፡ እንዳይሰማ (፪x)
ሕይወቴን ፡ ለውጧል ፡ ብርሃንህ ፡ በውስጤ
ብሩህ ፡ ተስፋ ፡ አያለሁ ፡ ለቀረው ፡ ዘመኔ
አቅጣጫን ፡ ለውጧል ፡ አላማህ ፡ በውስጤ
ብሩህ ፡ ተስፋ ፡ አያለሁ ፡ ለቀረው ፡ ዘመኔ

አዝ፦ ብርሃንህን ፡ በልቤ ፡ አብርተህልኛል
ጨለማዬን ፡ ሁሉ ፡ ገፈህልኛል
አቤቱ ፡ ከልቤ ፡ ላመስግንህ(፪x)
ኢየሱስ ፡ ከልቤ ፡ ላመስግንህ(፪x)