ትመለካለህ (Temelekaleh) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2013)
ርዝመት (Len.): 6:36
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Samuel Tesfamichael)

ገና ፡ ሰማይና ፡ ምድር ፡ ሳይፈጠር
ገና ፡ አማልክት ፡ የሚባል ፡ ሌላ ፡ ሳይኖር
ብቻህን ፡ በክብር ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ተቀምጠህ
ትመለካለህ! (፮x)

ክብር ፡ የሚለው ፡ ቃል ፡ ማንም ፡ ሳይከብርበት
አንተ ፡ ክብር ፡ ለብሰህ ፡ ዘለዓለም ፡ ኖርክበት
መክበር ፡ የሚለው ፡ ቃል ፡ ሌላ ፡ ሳይከብርበት
አንተ ፡ ክብርን ፡ ጠግበህ ፡ ዘለዓለም ፡ ኖርክበት

ክብር ፡ ራሱ ፡ የሚያውቀው ፡ አንተን ፡ ነው
መጀመሪያ ፡ የታወቀው ፡ በአንተ ፡ ነው
ክብር፡ ማለት ፡ የሚያውቀው ፡ አንተን ፡ ነው
መጀመሪያ ፡ የታወቀው ፡ በአንተ ፡ ነው
ክብር ፡ ራሱ ፡ የሚያውቀው ፡ አንተን ፡ ነው
መጀመሪያ ፡ የታወቀው ፡ በአንተ ፡ ነው

ትመለካለህ! እግዚአብሔር (፪x)
ኦሆሆ ! ኦኡዎ

ገና ፡ ፀሐይ ፡ ከዋክብት ፡ ሳይታሰቡ
ገና ፡ ነፋሳት ፡ ሳይወጡ ፡ ከመዛግብቱ
በአእላፋት ፡ መላዕክት ፡ ቀን ፡ ከሌት ፡ ተከበህ
ትመለካለህ (፮x)

ክብር ፡ የሚለው ፡ ቃል ፡ ማንም ፡ ሳይከብርበት
አንተ ፡ ክብር ፡ ለብሰህ ፡ ዘለዓለም ፡ ኖርክበት
መክበር ፡ የሚለው ፡ ቃል ፡ ሌላ ፡ ሳይከብርበት
አንተ ፡ ክብርን ፡ ጠግበህ ፡ ዘለዓለም ፡ ኖርክበት

ክብር፡ ማለት ፡ የሚያውቀው ፡ አንተን ፡ ነው
መጀመሪያ ፡ የታወቀው ፡ በአንተ ፡ ነው
ክብር፡ ራሱ ፡ የሚያውቀው ፡ አንተን ፡ ነው
መጀመሪያ ፡ የታወቀው ፡ በአንተ ፡ ነው
ክብር ፡ ማለት ፡ የሚያውቀው ፡ አንተን ፡ ነው
መጀመሪያ ፡ የታወቀው ፡ በአንተ ፡ ነው

እናመልክሃለን! እግዚአብሔር (፯x)