መልካም ፡ ነህ (Melkam Neh) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)
ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፪ (2009)
ርዝመት (Len.): 7:31
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Samuel Tesfamichael)

እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላመስግንህ ፡ ለእኔ ፡ ስላደረከው ፡ ሥራ
ከየት ፡ ጀምሬ ፡ ልዘርዝረው ፡ ልተርከው ፡ በየተራ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላመስግንህ ፡ ለእኔ ፡ ስላደረከው ፡ ሥራ
ከየት ፡ ጀምሬ ፡ ልዘርዝረው ፡ ልተርከው ፡ በየተራ

ቃላት ፡ ባጣ ፡ የቱን ፡ ጀምሬ ፡ እንደምጨርስ
ሁለንተናዬ ፡ አንተን ፡ ያመስግን ፡ ሥራህን ፡ ያወድስ
ኦ ፡ ቃላት ፡ ባጣ ፡ ከየት ፡ ጀምሬ ፡ እንደምጨርስ
ሁለንተናዬ ፡ አንተን ፡ ያመስግን ፡ ሥራህን ፡ ያወድስ

መልካም ፡ ነዉ ፡ እያሉ ፡ ዘመሩልህ ፡ ወንድሞቼ
መልካም ፡ ነዉ ፡ ልበልህ ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ
መልካም ፡ ነዉ ፡ እያሉ ፡ አዜሙልህ ፡ ወዳጆቼ
መልካም ፡ ነዉ ፡ ልበልህ ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ

ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው (፪x)
ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው (፪x)

ሰው ፡ ሁሉ ፡ ያውቀዋል
ከአንተ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግልኝ ፡ እንደሌለ
ሀገር ፡ ሁሉ ፡ ያውቀዋል
ከአንተ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግልኝ ፡ እንደሌለ
ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፫x)

በእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ሳለሁ ፡ አጥንቶቼም ፡ ሳይዋደዱ
ደፋ ፡ ቀና ፡ ስል ፡ አድጌ ፡ እግሮቼም ፡ ቆመው ፡ ሲሄዱ (፪x)

ሳልፈጠር ፡ የተፈጠሩ ፡ ቀኖቼን ፡ ያየህ
መልካም ፡ እየሆንክ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ እኔን ፡ እረዳህ (፪x)

መልካም ፡ ነዉ ፡ እያሉ ፡ ዘመሩልህ ፡ ወንድሞቼ
መልካም ፡ ነዉ ፡ ልበልህ ፡ እኔም ፡ ተስማምቼ
መልካም ፡ ነዉ ፡ እያሉ ፡ አዜሙልህ ፡ ወዳጆቼ
መልካም ፡ ነዉ ፡ አየሁህ ፡ እኔም ፡ በሕይወቴ

ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማድረግ ፡ የታወቀው (፪x)
ለእኔ ፡ መልካም ፡ በማሰብ ፡ የታወቀው (፪x)

ሰው ፡ ሁሉ ፡ ያውቀዋል
ከአንተ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግልኝ ፡ እንደሌለ
የሚያውቀኝ ፡ ያውቀዋል
ከአንተ ፡ በላይ ፡ መልካም ፡ የሚያደርግልኝ ፡ እንደሌለ
ሁልጊዜ ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነህ (፫x)

ተመስገን ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ተመስገን ፡ ልበልህ
ተመስገን ፡ ለዘለዓለም
ተመስገን (፪x)