From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ኀጢአተኛውን ፡ በፍቅር ፡ አይተህ
ከሕያውያን ፡ ጋር ፡ አንተ ፡ ቀላቅለህ
ካረከውማ ፡ ስምህን ፡ እንዲሸከም
ምን ፡ ትባላለህ ፡ ክበር ፡ ተመስገን
ስምህን ፡ እንዲሸከም ፡ አንተ ፡ ከአደረከው
አቤት ፡ ጌታዬ ፡ እወድሃለሁ
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ (፪x)
ሥምህን ፡ እንዲሸከም ፡ አንተ ፡ ከአደረከው
አቤት ፡ ጌታዬ ፡ ተገርሜያለሁ
ሥምህን ፡ እንዲሸከም ፡ አንተ ፡ ከአደረከው
አቤት ፡ ኢየሱስ ፡ ወድጄሃለሁ
ኃጢአተኛውን ፡ በፍቅር ፡ አይተህ
ከሕያውያን ፡ ጋር ፡ አንተ ፡ ቀላቅለህ
ካረከውማ ፡ ስምህን ፡ እንዲሸከም
ምን ፡ ትባላለህ ፡ ክበር ፡ ተመሥገን
ሥምህን ፡ እንዲሸከም ፡ አንተ ፡ ከአደረከው
አቤት ፡ ጌታዬ ፡ እወድሃለሁ
እወድሃለሁ ፡ እወድሃለሁ (፪x)
ሥምህን ፡ እንዲሸከም ፡ አንተ ፡ ከአደረከው
አቤት ፡ ጌታዬ ፡ ተገርሜያለሁ
ሥምህን ፡ እንዲሸከም ፡ አንተ ፡ ከአደረከው
አቤት ፡ ኢየሱስ ፡ ወድጄሃለሁ
ህመም ፡ ደዌዬን ፡ ተሸከመ
ያለ ፡ ኃጢአቱ ፡ ተገረፈ
በሰው ፡ ሁሉ ፡ ተጠላ ፡ ተናቀ
እንደጠፋ ፡ በግ ፡ ተቅበዝባዡን : እኔን ፡ ፍለጋ
ተጨነቀ ፡ ተሰቃየ
መስቀል ፡ ላይ ፡ ዋለ ፡ ደሙ ፡ ፈሰሰ
በትንሳኤው ፡ ሃይል ፡ ሕያው ፡ አደረገኝ
ከአብ: ጋር ፡ አስታርቆ ፡ ከጻድቃን ፡ ማህበር ፡ ቀላቀለኝ
ይመሥገን ፡ ይመሥገንልኝ (፬x)
ይመሥገን ፣ ይመሥገን ፣ ይመሥገን ፣ ይመሥገን
አዎ ፡ ይመሥገን ፡ (ይመሥገን)
ይመሥገንልኝ ፡ (ይመሥገን)
ጌታ ፡ ይመሥገን ፡ (ይመሥገን)
ይመሥገንልኝ ፡ (ይመሥገን) (፪x)
ሁሌ ፡ ይመስገን ፡ (ይመስገን)
ይመሥገንልኝ ፡ (ይመሥገን)
አዎ ፡ ይመሥገን ፡ (ይመሥገን)
ይመሥገንልኝ ፡ (ይመሥገን) (፫x)
ጌታ ፡ ይመሥገን ፡ (ይመሥገን)
ይመሥገንልኝ ፡ (ይመሥገን) (፪x)
ሁሌ ፡ ይመስገን ፡ (ይመስገን)
ይመሥገንልኝ ፡ (ይመሥገን)
|