From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አባቶች ፡ በእምነት ፡ አምልከውት ፡ አለፉ
ነቢያት ፡ አወሩለት ፡ መለከትን ፡ ነፉ
ሓዋሪያት ፡ የሰሙት ፡ በዐይናቸው ፡ ያዩት
በእጆቻችሀው ፡ ዳሰው ፡ የመሰከሩለት
መቃብር ፡ ፈንቅሎ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ የነሳው
እርሱን ፡ በማምለኬ ፡ እኔ ፡ እንጓደዳለሁ
ከሰማያት ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ያለ
በዘምናት ፡ መሃል ፡ እጅግ ፡ የከበረ
በሃይል ፡ በችሎቱ ፡ ዝናው ፡ የገነነ
በፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ የተመሰገነ
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው
ይሄ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ ይሄ ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ የማመልከው
አዝ፦ የማመልከው ፡ ይህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
የማደንቀው ፡ የምሰግድለት
እርሱ ፡ ብቻ ፡ የአማልክት ፡ አምላክ
የማመልከው ፡ ይህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
የማደንቀው ፡ የምሰግድለት
እግዚአብሔር ፡ የአማልክት ፡ አምላክ
ፀሐይን ፡ አቁሞ ፡ ጨረቃን ፡ ያዘገየ
አሰራሩ ፡ ልዩ ፡ ከሁሉ ፡ የተለየ
ባሕርን ፡ እንደግድግዳ ፡ እንደክምር ፡ ያደረገው
የጥንቱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዛሬም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው
አምላክስ ፡ ካሉ ፡ እንዲህ ፡ ነው
መኖር ፡ ካልቀረ ፡ እርሱ ፡ ነው
ካመለኩ ፡ አይቀር ፡ እርሱን ፡ ነው
አዝ፦ የማመልከው ፡ ይህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
የማደንቀው ፡ የምሰግድለት
እርሱ ፡ ብቻ ፡ የአማልክት ፡ አምላክ (፪x)
የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ ጣኦታቶች ፡ ናቸው
አይሰሙ ፡ አያዩ ፡ ቢጠሩ ፡ አይሰሟቸው
አምላካቸው ፡ ይቀስቀስ ፡ ተኝቷል ፡ ወይ ፡ ሲባል
እኔ ፡ የማመልከው ፡ በእሳት ፡ ይመልሳል
የተነሱበትን ፡ ሁሉ ፡ ያደቀቀ
በአሸናፊነቱ ፡ ግድሉ ፡ የታወቀ
ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው
አምላክስ ፡ ካሉ ፡ እንዲህ ፡ ነው
መኖር ፡ ካልቀረ ፡ እርሱ ፡ ነው
ካመለኩ ፡ አይቀር ፡ እርሱን ፡ ነው
አዝ፦ የማመልከው ፡ ይህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
የማደንቀው ፡ የምሰግድለት
እርሱ ፡ ብቻ ፡ የአማልክት ፡ አምላክ (፪x)
|