From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የከበረ ፡ ከሁሉ ፡ የተሻለ (፪x)
ሰውነቴን ፡ ለአንተ ፡ አቀርባለሁ (፪x)
እኔነቴን ፡ ለአንተ ፡ አቀርባለሁ (፪x)
መሰዊያን ፡ ሰራሁኝ ፡
ልሰዋልህ ፡ በፊትህ ፡ ላቀርበው
ያለኝን ፡ በሙሉ ፡ ታውቀዋለህ ፡
የቱን ፡ ነው ፡ ምትሻው
እያልኩኝ ፡ ስደረድር ፡
ምድርና ፡ ሞላዋ ፡
ለካስ ፡ የአንተ ፡ ነው
የሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡
ደስ ፡ እንዳያሰኝህ ፡
ይህንን ፡ ተረዳሁ
ታዲያ ፡ እኔ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ
ምኔን ፡ ሰጥቼ/ሰውቼ ፡ ደስ ፡ ላሰኝህ
እያልኩኝ ፡ ስጠይቅ ፡ ቃልህን
ስጠው/ሰዋው ፡ አለኝ ፡ እራስህን (፪x)
ስለዚህ ፡ እራሴን
ሕያውና ፡ ቅዱስ ፡ አድርጌ
ፊትህን ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘው
ፈቀድኩኝ ፡ ልሰዋ ፡ ይኸው
ልዩ ፡ ጣዕም ፡ የመዓዛ ፡ ሽታ
ሆኜ ፡ ልቅረብ ፡ በፊትህ ፡ ጌታ
ከሚቃጠል ፡ መስዋዕት ፡ ጋራ ፡ ወደፊትህ ፡ እመጣለሁ ፡ ኦሆሆ ኦሆሆ ሆሆ
የአምልኮዬ ፡ መዓዛ ፡ ሽታ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው ፡ ኦሆሆ ኦሆሆ ሆሆ
በምህረት ፡ የተሞላህ ፡ ታላቅ ፡ አምላክ ፡ ነህና ፡ ኦሆሆ
አሁንም ፡ አበዛለሁ ፡ ከነፍሴ ፡ ምሥጋና
ኦ ፡ በምሥጋና ፡
በዝማሬ ፡ እመጣለሁ
ኦሆሆ ፡ ወደ ፡ ማደሪያህ ፡ እገባለሁ (፮x)
|