ስውር ፡ እስሬን (Sewer Esrien) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 3.jpg


(3)

ምሳሌ ፡ የሌለህ
(Misale Yeleleh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ገመድ ፡ በአንገቴ ፡ ሳይገባ
እጅም ፡ ሰንሰለት ፡ ሳያስረው
እግሬ ፡ እየዘለለ ፡ አየተወራጨሁ
ታዲያ ፡ የምን ፡ እስራት ፡ ነው
ታዲያ ፡ የምን ፡ እስራት ፡ ነው

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስውር ፡ እስሬን ፡ አሳየኝ
እንዳልራመድ ፡ ያደረገኝ ፡ አሳየኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስውር ፡ እስሬን ፡ አሳየኝ
እንዳልራመድ ፡ ያደረገኝ ፡ አሳየኝ

ዓይኔ ፡ እያየ ፡ በሚያልፈው ፡ ላይ
እንዳልዘረጋ ፡ እጄን ፡ መዘዙን ፡ ሳላይ (እባክህ ፡ እርዳኝ)
እንድጋልብበት ፡ ሲያምረኝ ፡ ፈረሱ
ልጓም ፡ ከሌለው ፡ ይቅርብኝ ፡ እርሱ (፪x)

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስውር ፡ እስሬን ፡ አሳየኝ
እንዳልራመድ ፡ ያደረገኝ ፡ አሳየኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስውር ፡ እስሬን ፡ አሳየኝ
እንዳልራመድ ፡ ያደረገኝ ፡ አሳየኝ

ከንጉሥ ፡ ገበታ ፡ ከቃሉም ፡ ማዕድ
ሁሌም ፡ ማልጠፋ ፡ ሆኜ ፡ የንጉሥ ፡ ልጅ
ምነው ፡ መክሳቴ ፡ ምነው ፡ መመንመኔ
የዓለም ፡ ቤዛ ፡ ሆነኀኝ ፡ መድህኔ (፪x)

ገመድ ፡ ከአንገቴ ፡ ሸክም ፡ ከጫንቃዬ
ይሰበር ፡ የእግር ፡ ብረቱ
ይቆረጥ ፡ ከእጄ ፡ ሰንሰለቱ

ፍታልኝ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ
ፍታልኝ ፡ እስሬን ፡ ፍታልኝ
ፍታልኝ ፡ እባክህ ፡ ፍታልኝ
ፍታልኝ ፡ ውዴ ፡ ፍታልኝ (፪x)

ፍታልኝ ፡ ፍታልኝ
ኢየሱስ ፡ እስሬን ፡ ፍታልኝ
አባቴ ፡ አባቴ ፡ ፍታልኝ
ፍታልኝ