From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
betam
ኦሆሆሆ (፫x)
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ግርማህ ፡ አስፈሪ
የሌለህ ፡ አቻ ፡ ተወዳዳሪ ፡ ሆሆ ፡ ተወዳዳሪ
በትረ ፡ መንግሥትህ ፡ በዓለም ፡ የታወቀ
እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ሁሉን ፡ የበለጠ
ሆሆ ፡ ከሁሉም ፡ የላቀ (፪x)
ልዑል ፡ ሰማይ ፡ ዙፋንህ
ምድር ፡ መርገጫህ
ለግዛትህ ፡ ወሰን
የሌለህ ፡ ዳርቻ
ልዑል ፡ ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ
ልዑል ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ዙፋንህ
አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ይሁንልህ (፪x)
ይብዛልህ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ላብዛልህ ፡ ዕልልታዬ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ሥራዬ ፡ ይኸው
ምሥጋናዬ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው
አምልኮዬ ፡ ክቡር ፡ ሥምክን ፡ ያድምቀው (፪x)
ከምድር ፡ ጫፍ ፡ እስከ ፡ ጫፍ ፡ ቢሰበሰብ ፡ ፍጥረት
የሰማይ ፡ ሰራዊት ፡ እልፍ ፡ ጊዜ ፡ አላፋት
ሁሉም ፡ ተሰብሰቦ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ቢያወራ
ሊገልፅህ ፡ ቢሞክር ፡ በተራ ፡ በተራ
ምሳሌ ፡ የሌለህ ፡ ነህ ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ
ምሳሌ ፡ የሌለህ ፡ ነህ ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ (፪x)
ልዑል ፡ ሰማይ ፡ ዙፋንህ
ምድር ፡ መርገጫህ
ለገዛትህ ፡ ወሰን
የሌለህ ፡ ዳርቻ
ልዑል ፡ ለትልቅነትህ
ልዑል ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ
አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ይሁንልህ
ይብዛልህ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ላብዛልህ ፡ ዕልልታዬ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ሥራዬ ፡ ይኸው
ምሥጋናዬ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው
አምልኮዬ ፡ ክቡር ፡ ሥምህን ፡ ያድምቀው (፪x)
አቻ ፡ አጣሁልህ ፡ ወደር ፡ አጣሁልህ
መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ ፡ አጣሁልህ
አቻ ፡ አጣሁልህ ፡ ወደር ፡ አጣሁልህ
መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ ፡ አጣሁልህ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ የለም ፡ የሚመስልህ (፬x)
አቻ ፡ አጣሁልህ ፡ ወደር ፡ አጣሁልህ
መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ ፡ አጣሁልህ (፪x)
በሰማይ ፡ በምድር ፡ የለም ፡ የሚመስልህ (፬x)
አቻ ፡ አጣሁልህ ፡ ወደር ፡ አጣሁልህ
መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ ፡ አጣሁልህ (፪x)
በሰማይ ፡ በምድር ፡ የለም ፡ የሚመስልህ (፬x)
አንተ ፡ የከበርክበት ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያልክበት
የላቀ ፡ ሥልጣንህ ፡ ማነው ፡ የደረሰበት
ወልድ ፡ የተረከህ ፡ ሆይ ፡ ስለ ፡ ማንነትህ
ፅድቅ ፡ ነው ፡ ዙፋንህ ፡ ብርሃን ፡ አልባሳትህ
ምሳሌ ፡ የሌለህ ፡ ነህ ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ
ምሳሌ ፡ የሌለህ ፡ ነህ ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ (፪x)
ልዑል ፡ ሰማይ ፡ ዙፋንህ
ምድር ፡ መርገጫህ
ለገዛትህ ፡ ወሰን
የሌለህ ፡ ዳርቻ
ልዑል ፡ ለትልቅነትህ
ልዑል ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ
አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ይሁንልህ
ይብዛልህ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ላብዛልህ ፡ ዕልልታዬ
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ሥራዬ ፡ ይኸው
ምሥጋናዬ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው
አምልኮዬ ፡ ክቡር ፡ ስምህን ፡ ያድምቀው (፪x)
|