ክፉ ፡ ሳይመጣ (Kefu Saymeta) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 3.jpg


(3)

ምሳሌ ፡ የሌለህ
(Misale Yeleleh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ክፉ ፡ ሳይመጣ ፡ ከሩቅ ፡ አይተህ
ለልጅህ ፡ ሚስጥርን ፡ ትገልጣለህ
እንዳልጠፋ ፡ በንፋስ ፡ ማዕበሉ
ትታደገዋለህ ፡ ሆነህ ፡ መርከቡን

አዋቂ ፡ ነህ ፡ ሁሉንም ፡ አውቀኸዋል
የጥፋትን ፡ ውኃ ፡ ሰብስበሃል
የሞገዱን ፡ መናወጥ ፡ ዝም ፡ አሰኘህ
ለባሪያህ ፡ መልካምን ፡ አደረግህ

ብዙ ፡ ጐርፍ ፡ ተነስቶ ፡ ሕይወቴን ፡ ሊያጠፋ
ዕንቁዬን ፡ ሊያስጥለኝ ፡ ሊያስቆርጠኝ ፡ ተስፋ
ነፍሴን ፡ ያስጨነቀ ፡ ያናወጠ ፡ መከራ
ቀስ ፡ በቀስ ፡ እየገፋ ፡ አወጣኝ ፡ ወደ ፡ ተራራ
በእሳት ፡ ካልነጠረ ፡ ወርቅ ፡ እንደማይደምቀው
ያኔ ፡ እያስጨነቀኝ ፡ ለካ ፡ ለበጐ ፡ ነው
ያረጀው ፡ የደከመው ፡ እምነቴ ፡ በፀጋህ ፡ ታድሶ
በዝማሬ ፡ ተተካ ፡ የትላንቱ ፡ ለቅሶ

ሃሌሉያ (፫x)
ለታመነህ ፡ ሆነሀዋል ፡ መጠለያ
የተመካብህ ፡ አመለጠ ፡ በአንተ ፡ ጉያ

ሃሌሉያ (፫x)
የታመነህ ፡ ስንቱ ፡ ዳነ ፡ በአንተ ፡ ጉያ
የተመካብህ ፡ ስንቱ ፡ ዳነ ፡ በአንተ ፡ ጉያ
የታመነ ፡ አመለጠ ፡ በአንተ ፡ ጉያ