ክበር ፡ በሉት (Keber Belut) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 3.jpg


(3)

ምሳሌ ፡ የሌለህ
(Misale Yeleleh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ዓይኖቼን ፡ ወደተራሮች ፡ ባቀና
ረዳቴ ፡ ይመጣል ፡ ብዬ ፡ ደጅን ፡ ብጠና
ግን ፡ ተራራዎች ፡ መልስን ፡ ሰጡኝ ፡ በዝምታቸው
ሚስጥሩ ፡ ገባኝ ፡ እነርሱም ፡ እርዳታ ፡ እንደሚያሻቸው

ከታራራውም ፡ ላይ ፡ አሻቅቤ ፡ ሳይ ፡ በላይ ፡ በሠማይ
ረድኤቴ ፡ መጣ ፡ እይተራመደ ፡ በደመናት ፡ ላይ
እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ እንደሌለ ፡ ይህንን ፡ ስላየሁ
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ መኖሪያዬ ፡ አድርጌዋለሁ (፪x)

እንደተፈታች ፡ ሚዳቋ ፡ እንደተፈታች
እንደተፈታች ፡ እምቦሳ ፡ እንደተፈታች
ልውጣ ፡ ላይ ፡ ልውረድ ፡ ታች ፡ ነፍሴ ፡ ሃሴት ፡ ስላረገች
ቧረቀች ፡ ፈነደቀች ፡ ነፍሴ ፡ ሃሴት ፡ ስላረገች (፪x)

እስቲ ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ክበር
እስቲ ፡ ንገሥ ፡ በሉት ፡ ንገሥ
ጌታን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ክበር
ጌታን ፡ ንገሥ ፡ በሉት ፡ ንገሥ
እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሥሙ ፡ ሲወደስ
ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ (፪x)

ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ
ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥ
ይክበር ፡ ይክበር ፡ ይክበር
ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ

በእኔና ፡ በሞት ፡ መካከል ፡ አንድ ፡ እርምጃ ፡ ቀርቶ
እርሷንም ፡ ተራምዶ ፡ ውጦ ፡ ሊያስቀረኝ ፡ እጅጉን ፡ ጓግቶ
በጠላትም ፡ ሰፈር ፡ በቃ ፡ ሽንፈቴ ፡ ተረጋገጠ
ግን ፡ ረዳቴ ፡ መጣ ፡ በቅጽበት ፡ ነገሩ ፡ ተገለበጠ

ሊሰለጥንብኝ ፡ ባለው ፡ ቀን ፡ ጠላቴ ፡ ሰለጠንኩበት
ለእኔ ፡ በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ እርሱ ፡ ተቀበረበት
ድል ፡ አድራጊው ፡ ጌታ ፡ ድል ፡ እያደረገ ፡ በሰልፉ ፡ መሃል
በምሥጋና ፡ ነዶ ፡ በምርኮ ፡ ብዛት ፡ ያዘምረኛል/ያዘልለኛል (፪x)

እንደተፈታች ፡ ሚዳቋ ፡ እንደተፈታች
እንደተፈታች ፡ እምቦሳ ፡ እንደተፈታች
ልውጣ ፡ ላይ ፡ ልውረድ ፡ ታች ፡ ነፍሴ ፡ ሃሴት ፡ ስላረገች
ቧረቀች ፡ ፈነደቀች ፡ ነፍሴ ፡ ሃሴት ፡ ስላረገች (፪x)

እስቲ ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ክበር
እስቲ ፡ ንገሥ ፡ በሉት ፡ ንገሥ
ጌታን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ክበር
ጌታን ፡ ንገሥ ፡ በሉት ፡ ንገሥ
እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሥሙ ፡ ሲወደስ
ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ (፪x)

ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ (፫x)
ንገሥ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥ
ይክበር ፡ ይክበር ፡ ይክበር
ይንገሥ ፡ ይንገሥ ፡ ይንገሥ