ሃሌሉያ (Hallelujah) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 3.jpg


(3)

ምሳሌ ፡ የሌለህ
(Misale Yeleleh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሡ
ወደ ፡ ማደሪያው ፡ ይግባ ፡ ወደመቅደሱ (፪x)
ክበር ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ በምሥጋና
እጅግ ፡ ለተፈራው ፡ ለሆነው ፡ ገናና (፪x)
በመቅደሱ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አሰማለሁ ፡ በተራዬ
ከሚፈሩት ፡ ቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ እለዋለሁ ፡ ክበር
በመቅደሱ ፡ ምሥጋናዬን ፡ አሰማለሁ ፡ በተራዬ
ከሚፈሩት ፡ ቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ እለዋለሁ ፡ አምላኬ ፡ ክበር

ክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ክበር
ክበር ፡ ለዘለዓለም ፡ ክበር
ክበር ፡ ሁልጊዜ ፡ ክበር
ክበር ፡ ለዘለዓለም ፡ ክበር

የምህረት ፡ ደጁ ፡ ለእኔ ፡ ተከፍቶ
አየሁ ፡ የንጉሥ ፡ ዘንግ ፡ ደግሞ ፡ ተዘርግቶ
ከጨለማው ፡ ገዢ ፡ ነጥቆ ፡ አውጥቶ
ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ መንግሥት ፡ አስገባኝ ፡ ጐትቶ (፪x)

ሃሌሉያ ፡ አሃ (፬x)
ሃሌሉያ ፡ አሃሃ (፬x)

በምህረቱ ፡ ገባሁ ፡ ማን ፡ ሊከለክለኝ
ኢየሱስ ፡ ቤዛዬ ፡ አዳኝ ፡ ስለሆነኝ
ቅዱሱ ፡ ባለበት ፡ በውስጠኛው ፡ ስፍራ
አገልጋይ ፡ አደረገኝ ፡ ስሙን ፡ እንድጠራ (፪x)

ምህረቱ ፡ ከቦኛል ፡ በቅዱስ ፡ ደሙ ፡ አንጽቶኛል
ታዲያ ፡ ማነው ፡ የሚቃወመኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካጸደቀኝ
ምህረቱ ፡ ከቦኛል ፡ በቅዱስ ፡ ደሙ ፡ አንጽቶኛል
ታዲያ ፡ ማነው ፡ የሚኮንነኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካጸደቀኝ

ሃሌሉያ ፡ አሃ (፬x)
ሃሌሉያ ፡ አሃሃ (፬x)
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ኦሆሆ
ሃሌሉያ ፡ አሃሃ (፬x)