ኢየሱስ (Eyesus) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 3.jpg


(3)

ምሳሌ ፡ የሌለህ
(Misale Yeleleh)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2012)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ሕይወቴን ፡ ሰጥቼ ፡ ተከተልኩት
የነፍሴ ፡ ጌታ ፡ አደረኩት
ለመጪውም ፡ ዘመን ፡ እጣ ፡ ፈንታዬ
ላደርገው ፡ ወሰንኩኝ ፡ ከለላዬ
መላው ፡ እኔነቴን ፡ አስገዝቼ
መኖር ፡ ጀመርኩኝ ፡ ተደስቼ (፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ተጓደደች ፡ አምላኳን ፡ አግኝታ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ አለች ፡ ጠዋት ፡ ማታ (፪x)
ኢየሱስ (፬x) ፡ ኢየሱስ (፬x)

በተራራዎች ፡ ላይ ፡ እየዘለለ
በኮረብቶችም ፡ ላይ ፡ እየተወረወረ
ከፍታን ፡ ዝቅታን ፡ ሁሉ ፡ አልፎ
በመሃል ፡ ያለውን ፡ አሸንፎ
የውዴ ፡ ድምጽ ፡ ፈጥኖ ፡ ይመጣልኛል
ከአፉ ፡ ቃል ፡ ነፍሴን ፡ ያጠግባታል (፪x)

አዝ፦ ነፍሴ ፡ ተጓደለች ፡ አምላኳን ፡ አግኝታ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ አለች ፡ ጠዋት ፡ ማታ (፪x)
ኢየሱስ (፬x) ፡ ኢየሱስ (፬x)

ከማር ፡ ወለላ ፡ ይልቅ ፡ ይጣፍጠኛል
ሁሌ ፡ ስጠራህ ፡ ያስደንቀኛል
የማዐዛው ፡ ጠረን ፡ ሽታው ፡ አውዶኝ
በእርሱ ፡ ተስቤ ፡ ቤቱ ፡ ቀረሁኝ (፪x)

አገልጋይ ፡ ሆንኩኝ

ኢየሱስ (፬x) ፡ ኢየሱስ (፬x) ፡ ኢየሱስ (፬x)