ትለያለህ (Tileyaleh) - ሳሙኤል ተስፋሚካአኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ተስፋሚካአኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 4.jpg


(4)

መልህቄ
(Melhike)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፬ (2022)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6፡13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ተስፋሚካአኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

የክብር ንጉስ ሆይ እንዴት ታላቅ ነህ
ከዙፋንህ ስር በእውነት በመንፈስ ልስገድልህ

ከሰው ልጆች ይልቅ ያማረ ውበትህ
የፀጋ ቃል ሁሌ ያፈሳል ከንፈርህ
አይኖቼ አይተውህ
ፈዘዙ በክብርህ /2

ማን ሊመስልህ
አረ ማን ሊያክልህ
አንተ እኮ ከአማልክት ትለያለህ
ውዴ ከአእላፋት ትበልጣለህ

ፊትህ እንደ ፀሃይ በሃይል ያበራል
እንደ ብዙ ውሆች ድምፅህም ያስፈራል
በግርማህ ተገረሜ
ቀረሁኝ ተደምሜ

ማን ሊመስልህ
አረ ማን ሊያክልህ
አንተ እኮ ከአማልክት ትለያለህ
ውዴ ከአእላፋት ትበልጣለህ

ሃሌሉያ/8