From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ክንዳችሁ አይላላ
ጉልበታችሁ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ
የናዝሬቱ እየሱስ አለ ከእኛ ጋራ
ከግብፅ ከባርነት ከፈርዖን ብዛት
ህዝቡን ያሳረፈ ከጭንቀት ከፍርሃት
በእሳት በደመና በቀን ሌት የመራ
ያው የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ
መንገዱ እጅግ እሩቅ ቢመስል ሚከብድ ማያልቅ
የአለም ኑሮ ፈተና ቢሆንም ትንቅንቅ
ከእኛ ጋራ ያለው አለምን አሸንፏል
እስከ ፅዮን ድረስ በድል ይመራናል
ክንዳችሁ አይላላ
ጉልበታችሁ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ
አማኑኤል እርሱ አለ ከእኛ ጋራ
ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የወጡ ወደ ሰልፉ
የአንበሶችን አፍ ዘጉ የእሳትን ሃይል አጠፉ
በቅንም ፈረዱ መንግስታቱን ድል ነሱ
አለምን ኮነኑ ጣኦትን አፈረሱ
ዛሬም ከበውናል እነርሱ እንደደመና
ክንዳችን እንዳይላላ ጉልበታችን ይፅና
የፃድቅ ጉልበቱ ነውና እምነቱ
ቅዱሳን ካህናቱ እልፍ በሉ በርቱ
ክንዳችሁ አይላላ
ጉልበታችሁ አይበላ
የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ
ተስፋውን የሰጠው አለ ከእኛ ጋራ
ሃይልን በሚሰጠን ሁሉን እንችላለን
በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን
ክንዳችን ይበርታ ጉልበታችን ይፅና
አምላካችን ብርቱ ሁሉን ቻይ ነውና
|