From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዛሬማ ፡ ዓይኔ ፡ ያየው ፡ በለጠ ፡ ጆሮዬ ፡ ከሰማው
በላዬ ፡ ስለ ፡ ሾምኩህ ፡ ልቤን ፡ ኩራት ፡ አለው (፪x)
ንግሥናህን ፡ ሳስበው ፡ ውስጤ ፡ ተደንቀ ፡ መገረም ፡ ተሞላ
አንድ ፡ ነህ ፡ ለሕይወቴ ፡ አላውቅም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
የለኝም ፡ ከአንተ ፡ ሌላ
እንዴት ፡ ያምራል ፡ እንዴት ፡ ውብ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ወግህ ፡ ስርዓትህ ፡ ሆ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ያምራል ፡ እንዴት ፡ ውብ ፡ ነው
አገዛዝህ ፡ ቅን ፡ ነው ፡ ፍርድህ (፪x)
ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አትጠገብም (፬x)
ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አትጠገብም
ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልጠገብኩህም (፪x)
ማለዳም ፡ ማለዳ ፡ አዲስነትህ ፡ ነው ፡ ልዩ ፡ ያደረገህ
ዕድሜውን ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ፈጅቶ
የትኛው ፡ ሰው ፡ ለመደህ ፡ የትኛው ፡ ሰው ፡ ጠገበህ
ከትላንትናው ፡ ዛሬ ፡ ከዛሬው ፡ ነገ ፡ ይለያል ፡ የክብርህ ፡ ነፀብራቁ
ስለዚህ ፡ በልጠህብኛል ፡ ከአልማዝ ፡ ከወርቅ ፡ ከዕንቁ (፪x)
ጆሮዬ ፡ ድምጽን ፡ ሰምቶ ፡ አይጠግብም
ዓይኔ ፡ ክብርህን ፡ አይቶ ፡ አይጠግብም
ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ አውርቶ ፡ አይጠግብም
ቃላቴ ፡ አደናንቆህ ፡ አይጠግብም
ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አትጠገብም (፬x)
ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አትጠገብም
ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ አልጠገብኩህም (፪x)
እንዴት ፡ ያምራል ፡ እንዴት ፡ ውብ ፡ ነው
ንጉሥ ፡ ወግህ ፡ ስርዓትህ ፡ ሆ
ኧረ ፡ አንዴት ፡ ያምራል ፡ እንዴት ፡ ውብ ፡ ነው
አገዛዝህ ፡ ቅን ፡ ነው ፡ ፍርድህ (፪x)
ተወዳዳሪ ፡ አቻ ፡ እና ፡ እኩያ
የለህም ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለዘላለም (፬x)
|