ሥምህን ፡ ስጠራ (Semehen Setera) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 2.jpg


(2)

ግርማ ፡ ሞገስህ
(Germa Mogeseh)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 4:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ሥምህን ፡ ስጠራ ፡ በከንፈሮቼ
ደጋግመው ፡ ይለኛል ፡ መላው ፡ እኔነቴ
እስቲ ፡ ልደጋግመው ፡ ኢየሱሴ ፡ ብዬ
በረከቴ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ለነፍሴ ፡ ተድላዬ

ስደጋግመውማ (፪x)
ኑሮዬ ፡ ይባረካል ፡ ሰላሜ ፡ ይበዛልኛል
ኑሮዬ ፡ ይባረካል ፡ ደስታዬ ፡ ይበዛልኛል

እወድሃለሁ ፡ ስልህ ፡ ከልቤ ፡ እንደሆነ
አንተው ፡ ታውቀዋለህ (፪x)
እራስህ ፡ ታውቀዋለህ (፪x)
እከተላለው ፡ ስልህ ፡ ወስኜ ፡ እንደሆነ
ልቤን ፡ ታውቀዋለህ ፡ (፪x)
ውስጤንም ፡ ታውቀዋለህ (፪x)

የማይጠገብ ፡ ጣዕም ፡ የማያልቅ ፡ መዓዛዉ
ፍጥረት ፡ ተደነቀ ፡ ጌታዬን ፡ ስጠራዉ
እኔም ፡ አላረፍኩ ፡ አበዛሁ ፡ መጥራትን
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ኦሆ ፡ አዳኝ ፡ ነው ፡ ማለት

ስደጋግመውማ (፪x)
ደረቁ ፡ ይለመልማል ፡ አበባው ፡ ፍሬን ፡ ይሰጣል
ደረቁ ፡ ይለመልማል ፡ ቡቃያው ፡ ይሰጣል

እወድሃለሁ ፡ ስልህ ፡ ከልቤ ፡ እንደሆነ
አንተው ፡ ታውቀዋለህ (፪x)
እራስህ ፡ ታውቀዋለህ (፪x)

እከተላለው ፡ ስልህ ፡ ወስኜ ፡ እንደሆነ
ልቤን ፡ ታውቀዋለህ (፪x)
ውስጤንም ፡ ታውቀዋለህ (፪x)

በጠዋት ፡ በማታ ፡ ስሙን ፡ ሳነሳሳው
ለእኔ ፡ ድል ፡ ሆነኝ ፡ ለጠላት ፡ አበሳ
ኢየሱስ ፡ ስልበት ፡ ጠላት ፡ ተሸበረ
መንግስቱ ፡ ፈረሰ ፡ ወጥመድ ፡ ተሰበረ

ስደጋግመውማ (፪x)
ጠላቴ ፡ ይዋረዳል ፡ ሽንፈቱን ፡ ይከናንባል
ጠላቴ ፡ ይዋረዳል ፡ ምርኮዬን ፡ ይመልሰዋል

እወድሃለሁ ፡ ስልህ ፡ ከልቤ ፡ እንደሆነ
አንተው ፡ ታውቀዋለህ (፪x)
እራስህ ፡ ታውቀዋለህ (፪x)
እከተላለው ፡ ስልህ ፡ ወስኜ ፡ እንደሆነ
ልቤን ፡ ታውቀዋለህ (፪x)
ውስጤንም ፡ ታውቀዋለህ (፪x)