ሰማያት ፡ ያንጠባጠቡት (Semayat Yantebatebut) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 2.jpg


(2)

ግርማ ፡ ሞገስህ
(Germa Mogeseh)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ሰማያት ፡ ያንጠባጠቡት ፡ ዝናብ ፡ ቀላያትም ፡ የያዙት ፡ ውኃ
የምድርን ፡ ዛፎች ፡ ባስተባብር ፡ በደን ፡ ያሉ ፡ በበረሃ
አሃሃ ፡ ውኃው ፡ ቀለም ፡ ቢሆን ፡ አሃሃ ፡ ዛፉም ፡ ደግሞ ፡ ብዕር
አሃሃ ፡ ሁለቱም ፡ ቢጣመሩ ፡ አሃሃ ፡ ክብርህን ፡ እንዲያወሩ

አዝ፦ ብዕሬ ፡ እንኳን ፡ አንደበት ፡ ኖሮት ፡ ቢፈጠር
ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ ይናገር ፡ ነበር (፪x)

ተራ ፡ ንጉስ ፡ ቤት ፡ እንኳን ፡ ገብቼ
ስለእርሱና ፡ ዘሩ ፡ ቀለሜን ፡ በከንቱ ፡ ጨርሼ
ንጉሥ ፡ ዘውዱን ፡ ሲደፋ ፡ የጻፍኩት ፡ አኔው ፡ ሰምቼ
ሲሻር ፡ ሲዋረድ ፡ ፡ ተረኩት ፡ ደግሞ ፡ መልሼ

አሃሃ ፡ ሰልችቶኛል ፡ ስተርከው ፡ የምድሩን
አሃሃ ፡ ግራ ፡ ይገባኝ ፡ ሲሾሙና ፡ ሲሻሩ
አሃሃ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሰዎች ፡ የላዩን ፡ ብትጽፉብኝ
አሃሃ ፡ የምድሩን ፡ ከማውራት ፡ መተረክ ፡ ብትገላግሉኝ
አሃሃ ፡ ጥሜ ፡ እንዲረካ ፡ የልቤ ፡ እንዲደርስ
አሃሃ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ቀለሜን ፡ ስለእርሱ ፡ ብጨርስ

አዝ፦ ብዕሬ ፡ እንኳን ፡ አንደበት ፡ ኖሮት ፡ ቢፈጠር
ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ ይናገር ፡ ነበር (፪x)

ወዶ ፡ አፍቅሮ ፡ ሲያስብ ፡ ሰው ፡ በልቡ
ይጠበብብኛል ፡ ለመግለፅ ፡ የውስጥ ፡ ሃሳቡ
ወደድኩኝ ፡ ባለበት ፡ ቅፅበት ፡ ጠላሁ ደግሞ ፡ ይልብኛል
ወረት ፡ ያለው ፡ ፍቅር ፡ ለእኔስ ፡ ግራ ፡ ገብቶኛል

አሃሃ ፡ ሰልችቶኛል ፡ ስተርከው ፡ የምድሩን
አሃሃ ፡ ግራ ፡ ይገባኛል ፡ ስዋደዱ ፡ ሲጣሉ
አሃሃ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሰዎች ፡ የላዩን ፡ ብትጽፉብኝ
አሃሃ ፡ የምድሩን ፡ ከማውራት ፡ መተረክ ፡ ብትገላግሉኘ
አሃሃ ፡ ጥሜ ፡ እንዲረካ ፡ የልቤ ፡ እንዲደርስ
አሃሃ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ቀለሜን ፡ ስለእርሱ ፡ ብጨርስ

አዝ፦ ብዕሬ ፡ እንኳን ፡ አንደበት ፡ ኖሮት ፡ ቢፈጠር
ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ ይናገር ፡ ነበር (፪x)

ከድሮ ፡ ጀምሮ ፡ ሁኔታው ፡ የማይቀየር
እንዳለ ፡ የነበረ ፡ እንዲሁ ፡ ደግሞ ፡ የሚኖር
ጥንት ፡ ስለእርሱ ፡ የጻፍኩት ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልቀየርኩት
ከትውልድ ፡ ትውልድ ፡ ይሄው ፡ አሳለፍኩት

አሃሃ ፡ ስለመለወጡ ፡ ሁሌ ፡ የማልሰጋበት
አሃሃ ፡ ከሁሉ ፡ የተለየ ፡ ጽናትን ፡ ያየሁበት
አሃሃ ፡ ብጀምር ፡ ላወራ ፡ ስለእርሱ ፡ መስሎኝ ፡ አንደሰው
አሃሃ ፡ ቀለሜ ፡ አለቀ ፡ እንጂ ፡ እሱንማ ፡ መች ፡ ልጨርሰው
አሃሃ ፡ ብቀጥል ፡ ላወራ ፡ ስለእርሱ ፡ መስሎኝ ፡ እንደሰው
አሃሃ ፡ አኔ ፡ አለኩ ፡ እንጂ ፡ ዘመኑን ፡ መች ፡ ልጨርሰው

አዝ፦ ብዕሬ ፡ እንኳን ፡ አንደበት ፡ ኖሮት ፡ ቢፈጠር
ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ ይናገር ፡ ነበር (፪x)