ምስክር ፡ ነኝ (Meseker Negn) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 2.jpg


(2)

ግርማ ፡ ሞገስህ
(Germa Mogeseh)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 6:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

አዝ፦ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አምላክ ፡ እንደሆንክ
ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ጌታ ፡ እንደሆንክ
እመሰክራለሁ ፡ እንደምትረዳ
ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እንደምትደርስ ፡ ለተጐዳ

እኔን ፡ ያዩ ፡ ዓይኖችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም
እኔን ፡ የሰሙ ፡ ጆሮዋችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም
እኔን ፡ ያነሱ ፡ እጆችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም
እኔን ፡ ያጽናኑ ፡ ቃሎችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም

በሰማይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ከፍ ፡ ባለ ፡ ስፍራ
በምድር ፡ ሆኜ ፡ ትንሽ ፡ ሰው ፡ እርዳኝ ፡ ብዬ ፡ ስጣራ
ሰምተህ ፡ ከመለስከኝ ፡ ቀኝህ ፡ ከረዳችኝ
ላመስግን ፡ በዘመኔ ፡ ክንድህ ፡ ካገዘችኝ
ኦሆ ፡ ክንድህ ፡ ካገዘችኝ

አዝ፦ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አምላክ ፡ እንደሆንክ
ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ጌታ ፡ እንደሆንክ
እመሰክራለሁ ፡ እንደምትረዳ
ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እንደምትደርስ ፡ ለተጐዳ

እኔን ፡ ያዩ ፡ ዓይኖችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም
እኔን ፡ የሰሙ ፡ ጆሮዋችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም
እኔን ፡ ያነሱ ፡ እጆችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም
እኔን ፡ ያጽናኑ ፡ ቃሎችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም

ዮርዳኖስ ፡ ሲከፈል ፡ ተዓምር ፡ ማሳያ
ከመሃል ፡ ድንጋይ ፡ ወጣ ፡ ሆነ ፡ መታሰቢያ
እኔም ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ ሥራህን ፡ ስላየሁ
ሕያው ፡ ለመሆንህ ፡ ምስክር ፡ እሆናለሁ
ኦሆ ፡ ምስክር ፡ እሆናለሁ

እንኳን ፡ ወዳጆቼ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ ፡ እኔም ፡ ለእራሴ
አስቤው ፡ አላውቅም ፡ በህልሜም ፡ በውኔ (፪x)

ጠላቶቼማ ፡ የኔን ፡ ውድቀት ፡ የሚሹ
አሳፈርካቸዉ ፡ ታምራትህን ፡ አዩ (፪x)

በለቅሶ ፡ ተዘርቶ ፡ በደስታ ፡ ከታጨደ
በኩርንችት ፡ ፈንታ ፡ ባርሰነት ፡ ከበቀለ
ንጉሥ ፡ ለሚወደው ፡ ሰው ፡ እንዲህ ፡ ይደረጋል
ማይጠፋ ፡ ምልክት ፡ ነው ፡ ዓይኔ ፡ ይህን ፡ አይቷል
ኦሆ ፡ ዓይኔ ፡ ይህን ፡ አይቷል

አዝ፦ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አምላክ ፡ እንደሆንክ
ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ጌታ ፡ እንደሆንክ
እመሰክራለሁ ፡ እንደምትረዳ
ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እንደምትደርስ ፡ ለተጐዳ

እኔን ፡ ያዩ ፡ ዓይኖችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም
እኔን ፡ የሰሙ ፡ ጆሮዋችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም
እኔን ፡ ያነሱ ፡ እጆችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም
እኔን ፡ ያጽናኑ ፡ ቃሎችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም

እንኳን ፡ ወዳጆቼ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ ፡ እኔም ፡ ለእራሴ
አስቤው ፡ አላውቅም ፡ በህልሜም ፡ በውኔ (፪x)

ጠላቶቼማ ፡ የኔን ፡ ውድቀት ፡ የሚሹ
አሳፈርካቸዉ ፡ ታምራትህን ፡ አዩ (፪x)