From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ከጉባዔው ፡ መሃል ፡ ብዙ ፡ ሕዝብም ፡ ካለበት
ተጋባዥ ፡ ሰው ፡ ሆኜ ፡ ያኔ ፡ በፍርሃት
ህዝቡ ፡ ብዙ ፡ ግን ፡ ባንድ ፡ ድምፅ ፡ አቤት ፡ ዝማርያቸው
መፅሐፍ ፡ ተከፍቶ ፡ ይነገራል ፡ ሰምቼ ፡ ማላውቀው (፪x)
ከቃሉ ፡ የህይወት ፡ ውሃ ፡ ወደልቤ ፡ ፈሰሰ
ሳላቅማማ ፡ ጠጣሁት ፡ ውስጤም ፡ ረሰረስ
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ያለ ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዳግመኛ ፡ ተወለድኩኝ
በልቤ ፡ አምኝ ፡ በአፌም ፡ መሰከርኩኝ
በዚያን ፡ ቀን ፡ አሃሃ ፡ ታሪኬ ፡ ተቀየረ
በዚያን ፡ ቀን ፡ ኦሆሆ ፡ ቀንበሬ ፡ ተሰበረ
በዚያን ፡ ቀን ፡ ሽክሜም ፡ ቀለለልኝ
በዚያን ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አልኩኝ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ
አንተን ፡ መሳይ ፡ ወዳጅ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ መሃሪ
አንተን ፡ መሳይ ፡ አምላክ
ለማወቅ ፡ ተከፈቱ ፡ ዓይኖቼ
የመዳንን ፡ ቃል ፡ ሰምቼ
ወስኜ ፡ አንተን ፡ ያገኘሁባት
ያችን ፡ ቀን ፡ አልረሳት
ያችን ፡ ቀን ፡ ልባርካት (፪x)
ውዴ ፡ ደጁን ፡ ሲያንኳኳ ፡ በሬን ፡ ከፈትኩለት
ከእኔ ፡ ጋር ፡ እራት ፡ በላ ፡ የዋህ ፡ ነው ፡ በልቡ ፡ ትሁት
ተቆረሰ ፡ የሕይወት ፡ እንጀራ ፡ ዓይኖቼም ፡ ተከፈቱ
እንደንቦሳ ፡ ዘለልኩኝ ፡ አይረሳኝም ፡ ዕለቱ
በዚያን ፡ ቀን ፡ አሃሃ ፡ ኃጢያቴ ፡ ተሰረየ
በዚያን ፡ ቀን ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ ፡ ደስታ ፡ ሆነ
በዚያን ፡ ቀን ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ ተቀመጥኩኝ
በዚያን ፡ ቀን ፡ አምላክን ፡ እኔ ፡ ወረስኩኝ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ
አንተን ፡ መሳይ ፡ ወዳጅ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ መሃሪ
አንተን ፡ መሳይ ፡ አምላክ
ለማወቅ ፡ ተከፈቱ ፡ ዓይኖቼ
የመዳንን ፡ ቃል ፡ ሰምቼ
ወስኜ ፡ አንተን ፡ ያገኘሁባት
ያችን ፡ ቀን ፡ አልረሳት
ያችን ፡ ቀን ፡ ልባርካት (፪x)
ይገርማል ፡ እኔን ፡ መውደድህ ፡ ይገርማል
ይገርማል ፡ እኔን ፡ ማሰብህ ፡ ይገርማል (፪x)
ይገርማል ፡ እኔን ፡ መውደድህ
ይገርማል ፡ እኔን ፡ ማሰብህ
ይገርማል ፡ እኔን ፡ ማፍቀርህ ፡ ይገርማል (፫x)
|