ግልሙትናዋ (Gelmutenawa) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 2.jpg


(2)

ግርማ ፡ ሞገስህ
(Germa Mogeseh)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ግልሙትናዋ ፡ እጅግ ፡ ስለበዛ
ሥራዋ ፡ አይቆምም ፡ ጻዲቅ ፡ ካልተነሳ
የነብያትና ፡ የቅዱሳን ፡ ጠላት
ጻድቅ ፡ ታጥቀህ ፡ ውጣ ፡ እርሱዋን ፡ ተበቀላት

ኤልዛቤል ፡ ትዋረዳለች
ኤልዛቤል ፡ ውሾች ፡ ይበሏታል
ኤልዛቤል ፡ ትዋረዳለች
ኤልዛቤል ፡ ሥራዋ ፡ ይፈርሳል [1]

ጻዲቁ ፡ ሄደ ፡ ገሠገሰ (፬x)

በዚህ ፡ ዘመን ፡ ሕዝቡን ፡ ያራደ ፡ ያንቀጠቀጠ
እሱ ፡ ማን ፡ ነው (፫x)
የእግዚአብሔር ፡ የእቃ ፡ ጦር ፡ ለብሶ
ጻድቅ ፡ ይጋጠመው (፫x)

ጻዲቁ ፡ ሄደ ፡ ገሠገሰ (፬x)

ጉልበት ፡ ሆኖለታል ፡ እግዚአብሔር ፡ አምላኩ
በእምነት ፡ እሮጠ ፡ እየያ ፡ ፊት ፡ ፊቱ
አልተመለሰም ፡ ከቶ ፡ ወደ ፡ ኋላ
ተስፋው ፡ አምላኩ ፡ ነው ፡ አያይም ፡ ሌላ
(፪x)

በልዑል ፡ አምላክ ፡ ሥም ፡ ተማምኖ
በትከሻው ፡ መሃል ፡ አድሮ
ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ብሎ
ይኖራል ፡ ጌታውን ፡ አክብሮ

ጻዲቁ ፡ ሄደ ፡ ገሠገሰ (፬x)

የእግዚአብሔር ፡ ዓይኖች ፡ ያረፉበትን ፡ ሰው
ባዶ ፡ የምታደርግ ፡ የምታስቀር ፡ ላጭታው
አልያዝም ፡ የሚል ፡ ደግሞ ፡ የጨከነ
እርሷን ፡ የሚያዋርድ ፡ ጻድቅ ፡ ወዴት ፡ አለ

ደሊላ ፡ ትዋረዳለች
ደሊላ ፡ ጌታ ፡ ይበቀላታል
ደሊላ ፡ ትዋረዳለች
ደሊላ ፡ ሥራዋ ፡ ይፈርሳል

ደሙ ፡ በግንባሩ ፡ ሆኖ ፡ በመቃኑ
እንዳይነካ ፡ እምላክ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ለካ (፪x)

ጻዲቁ ፡ ሄደ ፡ ገሠገሰ (፬x)

  1. ፪ ነገሥት ፱ ፡ ፴ - ፴፭ (2 Kings 9:30-35)