ኢየሱስ (Eyesus) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 2.jpg


(2)

ግርማ ፡ ሞገስህ
(Germa Mogeseh)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

ልቤ ፡ አንተን ፡ ይላል
መንፈሴም ፡ ወዳንተ ፡ ይገሰግሳል
ጉጉቴ ፡ አንተን ፡ ማክበር ፡ ነው
ፍላጎቴ ፡ ክብርህን ፡ ማየት ፡ ነው

የእኔ ፡ ደስታ ፡ አንተን ፡ ማስደሰት ፡ ነው
ዓላማዬ ፡ የአንተ ፡ ዓላማ ፡ ነው
የእኔ ፡ ደስታ ፡ ደስ ፡ ሲልህ ፡ ማየት ፡ ነው
ዓላማዬ ፡ የአንተ ፡ ዓላማ ፡ ነው

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፪x)

ከምትወደው ፡ ጋራ ፡ እስማምለሁ
የምትጠላው ፡ ለኔ ፡ ጠላቴ ፡ ነው
በመታዘዝ ፡ ፍቅሬን ፡ እገልጻለሁ
ዝቅ ፡ ማለቴ ፡ አንተን ፡ ከፍ ፡ ላደርግ ፡ ነው

መኖር ፡ ትርጉም ፡ ሚስጥሩ ፡ አንተ ፡ ነህ
እወዳለሁ ፡ ዛሬም ፡ ልገዛልህ (፪x)

ዋላ ፡ ወደውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደሚናፍቅ
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ተጠማች
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ተጠማች (፪x)

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፪x)

እንደልብህ ፡ ሆኜ ፡ ልኑርልህ
ልቤን ፡ ትቼ ፡ ያየኸውን ፡ ልይልህ
መንፈስን ፡ ከኔ ፡ አትውሰደው
አጥፍ ፡ ልስገድ ፡ ሁሌም ፡ ላገልግለው

ከውሃ ፡ ውስጥ ፡ እንደወጣ ፡ ዓሣ
መኖር ፡ አልችልም ፡ ተለይቼ ፡ ጌታ (፪x)

ዋላ ፡ ወደውኃ ፡ ምንጭ ፡ እንደሚናፍቅ
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ተጠማች
ነፍሴ ፡ አንተን ፡ ተጠማች (፪x)

ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፪x)