እወድሃለሁ ፡ ወዳጄ (Ewedihalehu Wedajie) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 2.jpg


(2)

ግርማ ፡ ሞገስህ
(Germa Mogeseh)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 6:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

አዝእወድሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x)
እወድሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ
አፈቅርሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x)
አፈቅርሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ

መች ፡ ቀረሁ ፡ ስላንተ ፡ ሰምቼ
አወኩህ ፡ አንተ ፡ ተጠግቼ (፪x)
አልናከኝም ፡ ተቀብለኸኛል
ልጅህም ፡ ምክንያት ፡ ሆኖልኛል
ኢየሱስ ፡ ምክንያት ፡ ሆኖልኛል

ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሥምህን ፡ ለመጥራቴ ፡ አዎ (፪x)
ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ቤትህ ፡ ለመኖሬ ፡ አዎ (፪x)

በትንሿ ፡ ልቤ ፡ ስትገባ
መውደዴን ፡ ገለፅኩልህ ፡ በእንባ
ምን ፡ ልበል ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ልናገር
ከማምለክ ፡ ከማመስገን ፡ በቀር
ምን ፡ ልበል ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ልናገር

በትንሿ ፡ ልቤ ፡ ስትገባ
ማፍቀሬን ፡ ገለፅኩልህ ፡ በእንባ
ምን ፡ ልበል ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ልናገር
ለቃልህ ፡ ከመሸነፍ ፡ በቀር
ምን ፡ ልበል ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ልናገር

አዝእወድሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x)
እወድሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ
አፈቅርሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x)
አፈቅርሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ

ለፍቅሬ ፡ መግለጫ ፡ ቋንቋ ፡ ቢያጥረኝ ፡ እንኳን
ግን ፡ ላወራ ፡ ልናገረው ፡ ዝም ፡ ከማለት ፡ ቢሻል
የገረመኝ ፡ መዳኔ ፡ ነው ፡ እያልኩኝ ፡ ሳውራ
ድንቅህን ፡ አሳየኸኝ ፡ በዘመኔ ፡ በየተራ

ትገርማለህ ፡ ታስገርማለህ
ትገርማለህ ፡ አንተ
ትገርማለህ ፡ ታስገርማለህ
ትደንቃለህ ፡ አንተ

አዝእወድሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x)
እወድሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ
አፈቅርሃለሁ ፡ ወዳጄ (፪x)
አፈቅርሃለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ

አልቀረሁ ፡ ስላንተ ፡ ሰምቼ
አወኩህ ፡ አንተ ፡ ተጠግቼ (፪x)
አልናከኝም ፡ ተቀብለኸኛል
ልጅህም ፡ ምክንያት ፡ ሆኖልኛል
ኢየሱስ ፡ ምክንያት ፡ ሆኖልኛል

ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ልጅህ ፡ ለመሆኔ ፡ አዎ (፪x)
ምክንያቱ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ አባት ፡ ለማግኘቴ ፡ አዎ (፪x)