በጥበብህ ፡ በችሎታህ (Betebebih Bechelotah) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 2.jpg


(2)

ግርማ ፡ ሞገስህ
(Germa Mogeseh)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

በጥበብህ ፡ በችሎታህ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው ፡ ጌታ (፪x)
ዕውቀትህ ፡ የተለየ ፡ ፍጥረት ፡ እንዳንተ ፡ አልሰማ ፡ አላየ (፪x)

(አሃሃ) ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ብልህም
(አሃሃ) ፡ ከዚያም ፡ ትልቃለህ
(አሃሃ) ፡ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር
(አሃሃ) ፡ በማን ፡ ልመስልህ
 
ከምልህ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፬x)

ሰው ፡ ከፍታ ፡ መጨረሻ ፡ መርገጫህ ፡ ነው ፡ ላንተ ፡ መነሻ (፪x)
ታች ፡ ብወርድ ፡ ላይ ፡ ቢወጣ ፡ የሚመስልህ ፡ አንድም ፡ ታጣ
ታች ፡ ብወርድ ፡ ላይ ፡ ቢወጣ ፡ የሚያህልህ ፡ አንድም ፡ ታጣ

(አሃሃ) ፡ ከህዝብህ ፡ ጋር ፡ ሆኜ
(አሃሃ) ፡ ስምህን ፡ ባውድስ
(አሃሃ) ፡ እንኳን ፡ ልጨርሰው
(አሃሃ) ፡ ከመሃሉም ፡ እልደርስ

ጥበብህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)
ዕውቀትህ ፡ ሠፊ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)

ገዢዎችን ፡ ትሾማለህ ፡ ሲያሻህ ፡ ደግሞ ፡ ታወርዳለህ
ገዢዎችን ፡ ትሾማለህ ፡ ሲያሻህ ፡ ደግሞ ፡ ትሽራለህ
ልዕልናህ ፡ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ካንተ ፡ በላይ ፡ ማንም ፡ የለ (፪x)

(አሃሃ) ፡ ከህዝብህ ፡ ጋር ፡ ሆኜ
(አሃሃ) ፡ ስምህን ፡ ባውድስ
(አሃሃ) ፡ እንኳን ፡ ልጨርሰው
(አሃሃ) ፡ ከመሃሉም ፡ እልደርስ

ከምልህ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)
ልገልፅህ ፡ አልችልም ፡ የኔ ፡ ጌታ (፪x)

ላምልክ ፡ እንደገና ፡ አሃ (፫x)
አምላኬ ፡ ነህና
ላንግሥ ፡ እንደገና ፡ አሃ (፫x)
ንጉሤ ፡ ነህና (፪x)