በሰማይ ፡ በምድር (Besemay Bemeder) - ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል
(Samuel Tesfamichael)

Samuel Tesfamichael 2.jpg


(2)

ግርማ ፡ ሞገስህ
(Germa Mogeseh)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የሳሙኤል ፡ ተስፋሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Samuel Tesfamichael)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ የከበርከው
ከጥንትም ፡ ጀምሮ ፡ የነበርከው (፪x)

ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ የፀና
እግዚአብሔር ፡ ብቻህን ፡ ገናና (፫x)
ገናና ፡ ብቻህን ፡ ገናና
ገናና ፡ ብቻህን ፡ ነህ ፡ ገናና

ለሁሉም ፡ ምዕራፍ ፡ መጀመሪያቸው
መውጣትና ፡ መግባት ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ነው
ባለዝና ፡ ነህ ፡ ሁሉም ፡ ያውቅሃል
ገናናነትህ ፡ ደግሞ ፡ ዓለምን ፡ ሞልቷል

የከበረ ፡ የነገስህ ፡ ከፍ ያልህ ፡ የበረታህ
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)
አምላኬ ፡ ብቻ ፡ ጌታ ፡ ነህ (፪x)

በሰማይ ፡ በምድር ፡ የከበርከው
ከጥንትም ፡ ጀምሮ ፡ የነበርከው (፪x)

ዙፋንህ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ የፀና
እግዚአብሔር ፡ ብቻህን ፡ ገናና (፫)
ገናና ፡ ብቻህን ፡ ገናና
ገናና ፡ ብቻህን ፡ ነህ ፡ ገናና

አማልክት ፡ ተብለው ፡ እጅግ ፡ ተፈርተው
የሰዎች ፡ ሥራዋች ፡ ፍጡር ፡ ፈጥሩዋችው
አይሰሙ ፡ አያዩ ፡ ደግሞ ፡ አይመልሱ
ላወዳድርህ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ አንተን ፡ ከእነሱ

ከእንግዲህ ፡ በእኔ ፡ ዘር ፡ ከኔ ፡ በኋላ
አይመለክም ፡ ካንተ ፡ ሌላ
አይመለክም ፡ ካንተ ፡ ሌላ (፪x)

ወደር ፡ የሌለህ ፡ አቻ ፡ የሌለህ
መሳይ ፡ የሌለህ ፡ አቻ ፡ የሌለህ (፪x)

ሰማይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ምድር ፡ የምትረግጥ
ትላንት ፡ ዛሬ ፡ ነገ ፡ የማትለወጥ
እረጅምና ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ዙፋንህ
የማይቆጠር ፡ ነው ፡ እድሜ ፡ ዘመንህ

ከእንግዲህ ፡ በእኔ ፡ ዘር ፡ ከኔ ፡ በኋላ
አይሰበክም ፡ ካንተ ፡ ሌላ (፪x)
ከእንግዲህ ፡ በእኔ ፡ ዘር ፡ ከኔ ፡ በኋላ
አይለመንም ፡ ካንተ ፡ ሌላ (፪x)

ሌላ ፡ አይለመንም ፡ ካንተ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ አይለመንም ፡ ካንተ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ከብሮ ፡ አይታይም ፡ ካንተ ፡ ሌላ
ሌላ ፡ ሌላ ፡ ነግሶ ፡ አይታይም ፡ ካንተ ፡ ሌላ

ወደር ፡ የሌለህ ፡ አቻ ፡ የሌለህ
መሳይ ፡ የሌለህ ፡ አቻ ፡ የሌለህ (፪x)