መንፈሳዊ ፡ ዜና - Christian News

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በዚህ ፡ ገጽ ፡ ላይ ፡ እንዲቀርብ ፡ የሚፈልጉት ፡ መንፈሳዊ ፡ ነክ ፡ የሆኑ ፡ ዜናዎችን ፡ ለመላክ ፡ እዚህ ፡ ይጫኑ


አዲስ ፡ አልበም ፡ በሳሙኤል ፡ ንጉሤ
ሳሙኤል ፡ ንጉሤ
(Samuel Negussie)

Samuel Negussie 1.jpg

በእግዚአብሔር ፡ ዓለም (፳ ፻ ፯)
BeEgziabhier Alem (2014)
ዘማሪ ፡ ሳሙኤል ፡ ንጉሤ ፡ ፩ኛውን ፡ አልበም ፡ በጥር ፡ ፲፭ (January 23, 2015)፡ በዩጐ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ምርቃት ፡ ዝግጅት ፡ በይፋ ፡ ላይ ፡ ወጥቷል። ይህ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ዓለም ፡ የተባለውን ፡ አልበም ፡ ገዝተው ፡ ያዳምጡት ።፲፱ ጥር ፳ ፻ ፯ (January 27, 2015)ቃለ ፡ መጠይቅ ፡ ከዘማሪ ፡ ይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ ጋር
(Interview with Gospel Singer Yidnekachew Teka)
Location: Ethiopia
When: October 16, 2014
Where: Rise and Shine Show
በዝማሪ ፡ አገልግሎቱ ፡ የታወቀው ፡ ይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ በቅርብ ፡ ጊዜ ፡ ከራይዝ ፡ አንድ ፡ ሻይን ፡ ሾው ፡ ያደረገውን ፡ ቃለ ፡ መጠይቅ ፡ ከዚ ፡ በታች ፡ ማዳመጥ ፡ ይችላሉ ። በዝግጅቱ ፡ ይድነቃቸው ፡ ተካ ፡ ስለ ፡ አገልግሎቱ ፡ አንዲሁም ፡ እንዴት ፡ እዚህ ፡ ደረጃ ፡ እንደደረሰ ፡ ይገልጻል ። ሁላችንም ፡ እንዲሁም ፡ አገልጋዮች ፡ እንዲበረታቱበት ፡ ትምህርት ፡ ይሆናል ፡ በማለት ፡ እዚህ ፡ አቅርበነዋል ።

የይድነቃቸው ፡ ተካን ፡ የመጀመሪያ ፡ አልበም ፡ ቸኮለብኝ ፡ ልቤ ፡ ሊያገኝህ ፡ ሲባል ፡ የመዝሙር ፡ ግጥሞቹን ፡ ለማግኘት ፡ እዚህ ፡ ጫኑ


፲፬ ኅዳር ፳ ፻ ፯ (November 20, 2014)ቃለ ፡ መጠይቅ ፡ ከሙዚቃ ፡ አቀናባሪ ፡ ካሙዙ ፡ ካሳ ፡ እና ፡ ባለቤቱ ፡ ትዕግሥት ፡ ወይሶ
(Interview with Music Producer Kamuzu Kassa and Singer Tigist Woyesso)
Location: Ethiopia
When: November 02, 2014
Where: Yawdah Tv Show
በሙዚቃ ፡ አቀናባሪነቱ ፡ እውቅናን ፡ ያገኘው ፡ ካሙዙ ፡ ካሳ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ መመለሱን ፡ በያውዳህ ፡ የቴሌቪዢን ፡ ፕሮግራም ፡ ላይ ፡ በመገኘት ፡ ባደረገው ፡ ቃለ ፡ ምልልስ ፡ ተናግሯል ። ካሙዙ ፡ ካሳም ፡ በዚህ ፡ አጋጣሙ ፡ የዓለማዊ ፡ ሙዚቃ ፡ አቀናባሪነቱን ፡ ማቆሙን ፡ ገልጿል ። በተጨማሪም ፡ ዘፋኝ ፡ ትዕግሥት ፡ ወይሶ ፡ የእርሱ ፡ ባለቤት ፡ ስትሆን ፡ እርሷም ፡ እንዲሁ ፡ የዓለማዊ ፡ ሙዚቃ ፡ ዘፋኝነቷን ፡ ማቆሟን ፡ ለመመስከር ፡ ችላለች ። በዚህ ፡ አጋጣሚም ፡ ከ፲ ፡ ወር ፡ በፊት ፡ በቀድሞ ፡ ዘፋኝነቱ ፡ እጅግ ፡ ይታወቅ ፡ የነበረው ፡ ጥበቡ ፡ ወርቅዬ ፡ በዚሁ ፡ ዝግጅት ፡ ላይ ፡ በመገኘት ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ መምጣቱን ፡ እንዲሁም ፡ ዘፋኝነቱን ፡ እንዳቆመ ፡ ለመመስከር ፡ እንደቻለ ፡ እናስታውሳቹሃለን ። የካሙዙ ፡ ካሳና ፡ የጥበቡ ፡ ወርቅዬን ፡ ቃለ ፡ ምልልስ ፡ ቪዲዮዎች ፡ ከዚህ ፡ በታች ፡ ያገኟቸዋል ።

፳፮ ጥቅምት ፳ ፻ ፯ (November 05, 2014)አዲስ ፡ አልበም ፡ በአይዳ ፡ አብርሃም
አይዳ ፡ አብርሃም
(Ayda Abraham)

Ayda Abraham 1.jpg

ስላንተ (፳ ፻ ፯)
Selante (2014)
አይዳ ፡ አብርሃም ፡ አዲስ ፡ አልበም ፡ በቅርብ ፡ ቀን ፡ በገበያ ፡ ላይ ፡ ውሏል ። ይህ ፡ ስላንተ ፡ ተብሎ ፡ የተሰየመው ፡ ፩ኛው ፡ በጥቅምት ፰ ፡ ፳ ፻ ፯ ቀን (October 18, 2014) ፡ ምርቃት ፡ ዝግጅት ፡ ተደርጐ ፡ በይፋ ፡ ተለቋል ። በአይ-ቱንስ (iTunes) ላይ ፡ መሸጥ ፡ ሲጀምር ፡ አድራሻውን ፡ በዚህ ፡ ዜና ፡ ገጽ ፡ ላይ ፡ እንዲሁም ፡ በመዝሙር ፡ ሱቃችን ፡ ላይ ፡ እናወጣሎታልን ። ለጊዜው ፡ ከአልበሟ ፡ ነጠላ ፡ ዝማሬ ፡ ቪዲዮ ፡ ከዚህ ፡ በታች ፡ ማዳመጥ ፡ ይችላሉ ።፰ ትቅምት ፳ ፻ ፮ (October 18, 2014)ቃለ ፡ መጠይቅ ፡ ከእንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ ጋር
(Interview with Endalkachew Hawaz)
Location: Ethiopia
When: October 05, 2014
Where: Kiya Talk Show
በቅርቡ ፡ ቀን ፡ ዘማሪ ፡ እንዲሁም ፡ የሙዚቃ ፡ አስተማሪ ፡ የሆነው ፡ እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ በኪያ ፡ ሾው ፡ ላይ ፡ በመገኘት ፡ ቃለ ፡ መጠይቅ ፡ አድርጓል ። ኪያ ፡ ሾው ፡ በክርስቲያናዊ ፡ በሁኑ ፡ ርዕሶች ፡ ላይ ፡ ሰዎችን ፡ ቃለ ፡ መጠይቅ ፡ የሚደረግበት ፡ ዝግጅት ፡ ሲሆን ፡ በአብይ ፡ ታደለና ፡ በኤልሻዳይ ፡ ቴሌቪዥን ፡ ጣቢያ ፡ ጋር ፡ በትብብር ፡ የሚቀርብ ፡ ፕሮግራም ፡ ነው ። እንዳልካቸው ፡ ሃዋዝ ፡ ክብርህን ፡ አሳየኝ ፡ ስለተባለው ፡ አዲሱ ፡ አልበሙ ፡ እንዲሁም ፡ ስለዝማሬና ፡ ክርስቲያናዊ ፡ አገልግሎት ፡ ያለውን ፡ ሃሳብ ፡ በቃለ ፡ ምልልሱ ፡ ያካፍላል። ሙሉ ፡ ቃለ ፡ ምልልሱን ፡ ከዚህ ፡ በታች ፡ መመልከት ፡ ይችላሉ።

፴ መስከረም ፳ ፻ ፯ (October 10, 2014)የመጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ ትርጉም ፡ አገልግሎት ፡ በኢትዮጵያ
(Bible Translation in Ethiopia)
Location: Ethiopia
When: End of 2015
Where: Ethiopian Bible Society
በአሁኑ ፡ ወቅት ፡ በኢትዮጵያ ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ መስፋፋት ፡ አገልግሎት ፡ ሙሉ ፡ በሙሉ ፡ ተተርጉሞ ፡ ያለቀው ፡ በአምስት ፡ ቋንቋዎች ፡ ብቻ ፡ ነው ። በኢትዮጵያ ፡ ወደ ፡ ፹ (80) ፡ የሚጠጉ ፡ የተለያዩ ፡ ቋንቋቆች ፡ ይገኛሉ ። ሙሉ ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ (ብሉይና ፡ አዲስ ፡ ኪዳን) ፡ ተተርጉሞ ፡ የቀረበው ፡ በአማርኛ ፣ በትግርኛ ፣ በኦሮምኛ ፣ በወላይትኛ ፡ እና ፡ በጉራግኛ ፡ ቋንቋዎች ፡ ነው ። እነዚህም ፡ ቋንቋዎች ፡ ወደ ፡ ፶፭ ፡ በመቶ (55%) ፡ የሚሆነውን ፡ ሕዝብ ፡ እንደሚሸፍኑ ፡ ይነገራል ። አዲስ ፡ ኪዳን ፡ ብቻ ፡ ከ፳ (20) ፡ በላይ ፡ በሚሆኑ ፡ ቋንቋዎች ፡ ይገኛል ። ይህም ፡ ወደ ፡ ፹፭ ፡ በመቶ (85%) ፡ የሚሆነውን ፡ ሕዝብ ፡ ይሸፍናል ።

የኢትዮጵያ ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ ማህበር ፡ በሚቀጥለው ፡ ዓመት ፡ ሙሉ ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስን ፡ በሰባት ፡ ተጨማሪ ፡ ቋንቋዎች ፡ አዘጋጅቶ ፡ እንደሚያጠናቀቅ ፡ ገልጿል ። እነኚህ ፡ ቋንቋዎች ፡ አኟክ ፣ አፋር ፣ ሲዳማ ፣ ሃዲያ ፣ ካምባታ ፣ ኮንሶ ፡ እና ፡ ማሌ ፡ ናቸው ። በዚህ ፡ ሰዓት ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ ያልሰሙ ፡ እንዲሁም ፡ ቃሉን ፡ በቋንቋቸው ፡ ማንበብ ፡ ለማይችሉት ፡ ሰዎች ፡ በጸሎት ፡ እንዲሁም ፡ ባሎት ፡ አቅም ፡ የኢትዮጵያ ፡ የመጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ ማህበርን ፡ ለመርዳት ፡ ከፈለጉ ፡ እዚህ ፡ ጋር ፡ ይጫኑ


፳፮ ነሃሴ ፳ ፻ ፮ (August 31, 2014)የሕያው ፡ ቃል ፡ እና ፡ ቃል ፡ አምላክ ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ አፖች ፡ ተለቅቀዋል
(Hiyaw Qal & Qal Amlak Bible Apps for Android Released)
Amharic Bible App 1.jpg
Location: Android (Google Play)
When: August 19, 2014
Where: ሕያው ፡ ቃል (አማርኛ)

ቃል ፡ አምላክ (ትግርኛ)

ሕያው ፡ ቃል ፡ እና ፡ ቃል ፡ አምላክ ፡ ፫ ፡ እትም ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ አፖች ፡ በአንድሮይድ ፡ ጉግል ፡ ፕሌይ (Google Play) ፡ ላይ ፡ ተለቅቀዋል ። እነኚህ ፡ ነጻ ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱሶች ፡ በአማርኛ ፡ እና ፡ በትግርኛ ፡ ቋንቋ ፡ ቀርበውላችኋል ። በተጨማሪም ፡ የብሉይ ፡ ኪዳን ፡ እና ፡ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ መጽሐፎችን ፡ ያካትታሉ ።

ይህ ፡ እትም ፡ እንደ ፡ አፕል ፡ እትሙ ፡ ትልልቅ ፡ ለውጦችን ፡ ያካትታል፡-

  • የንጉሥ ፡ ያዕቆብ (King James) ፡ እና ፡ የዓለም ፡ እንግሊዘኛ (World English) ፡ ትርጉሞች
  • በአንድ ፡ ንኪ ፡ ብቻ ፡ ትርጉሞችን ፡ መለወጥ ፡ መቻል
  • አንዴ ፡ ሁሉንም ፡ ጽሁፍ ፡ አውርዶ ፡ ለማይት ፡ መቻል
  • ቃላትን ፡ መፈለግ ፡ መቻል (አንድ ፡ ቃል ፡ ወይም ፡ ቃላቶችን ፡ መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ ውስጥ ፡ መፈለግ)
  • የራስዎን ፡ ማስታወሻ ፡ መጻፍ
  • ያነበቡትን ፡ ክፍሎች ፡ ታሪክ ፡ ማግኘት ፣ ወዘተ

ከዚህ ፡ በታች ፡ የመጽሐፍ ፡ ቅዱሶቹን ፡ ዓይነቶቹን ፡ ሁሉ ፡ መገኛ ፡ ዝርዝር ፡ ይመልከቱ፡-


፲፰ ነሐሴ ፳ ፻ ፮ (August 24, 2014)ኢትዮጵያውያን ፡ መዘምራን ፡ ለአፍሪካ ፡ መዝሙር ፡ ሽልማት ፡ ተመረጡ
(Ethiopian Singers Nominated for the African Gospel Music Awards)
Location: London, England
When: Until August 24 2014
Where: http://agma2014.polldaddy.com
ሶስት ፡ ኢትዮጵያውያን ፡ መዘምራን ፡ በቅርቡ ፡ ለሚካሄደው ፡ አህጉር ፡ አቀፍ ፡ የአፍሪካ ፡ መዝሙር ፡ ሽልማት ፡ ዝግጅት (African Gospel Music Award) ፡ ታጭተዋል ። ምርጥ ፡ የምሥራቅ ፡ አፍሪካ ፡ ዘማሪ ፡ ለሚባለው ፡ ምድብ ፡ ሽልማት ፡ የታጩት ፡ መዘምራን ፡ የሚከተሉት ፡ ናቸው ፡-

የዚህን ፡ ዝግጅት ፡ አሸናፊዎች ፡ ለመወሰን ፡ የሰው ፡ ድምጽ ፡ እየተቀበሉ ፡ ነው ። ድምጽ ፡ ስብሰባው ፡ በ ፲፰ ነሐሴ ፳ ፻ ፮ (August 24, 2014) ፡ ይጠናቀቃል ። እርሶም ፡ ፩ ፡ ደቂቃ ፡ ወስደው ፡ በዚህ ፡ ድረ ፡ ገጽ ፡ በቀጥታ ፡ ድምጽዎን ፡ መስጠት ፡ ይችላሉ ። ከዛሬ ፡ ሁለት ፡ ዓመት ፡ በፊት ፡ ዘማሪ ፡ ዳዊት ፡ ጌታቸው ፡ በዚህ ፡ ዝግጅት ፡ ምርጥ ፡ የምሥራቅ ፡ አፍሪካ ፡ ዘማሪ ፡ በመባል ፡ ተመርጦ ፡ እንደተሸለመ ፡ ይታወሳል ። እኛም ፡ በዚህ ፡ ዓመት ፡ ለታጩት ፡ መዘምራን ፡ መልካም ፡ እድል ፡ እንመኛለን ።


፳፮ ሐምሌ ፳ ፻ ፮ (August 2, 2014)የመዝሙር ፡ ዝግጅት ፡ በዳዊት ፡ ጌታቸው
(Concert by Dawit Getachew)
የመስቀሉ ፡ ፍቅር
Artist: ዳዊት ፡ ጌታቸው
(Dawit Getachew)
Location: San Diego, CA, USA
When: August 3 2014
Where: Joan B. Kroc Theater
6611 University Avenue

Dawit Getachew August 3 2014.jpg


፲፪ ሐምሌ ፳ ፻ ፮ (July 19, 2014)


አዲስ ፡ አልበም ፡ በእንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ
እንዳልካቸው ፡ ሐዋዝ
(Endalkachew Hawaz)

Endalkachew Hawaz 5.jpg

ክብርህን ፡ አሳየኝ (፳ ፻ ፮)
Kebrehen Asayegn (2014)
እንዳልካቸው ፡ 'አናዋ' ፡ ሐዋዝ ፡ አዲስ ፡ አልበም ፡ በቅርብ ፡ ቀን ፡ በገበያ ፡ ላይ ፡ ውሏል ። ይህ ፡ ክብርህን ፡ አሳየኝ ፡ ተብሎ ፡ የተሰየመው ፡ ፭ኛው ፡ አልበም ፡ በሰሜን ፡ አሜሪካና ፡ በአውሮፓ ፡ ባሉት ፡ አገሮች ፡ እንደ ፡ አውሮፓውያን ፡ አቆጣተር ፡ June 2014 ፡ መሸጥ ፡ ጀምሯል ። በኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ደግሞ ፡ August 2014 ፡ መሸጥ ፡ ይጀምራል !፲፩ ሐምሌ ፳ ፻ ፮ (July 18, 2014)አዲስ ፡ አልበም ፡ በዶ/ር ፡ ለዓለም ፡ ጥላሁን
ዶ/ር ፡ ለዓለም ፡ ጥላሁን
(Lealem Tilahun)

Lealem Tilahun 3.jpg

የናርዶስ ፡ ሽቶዬ (፳ ፻ ፮)
Yenardos Shetoyie (2014)
ዶ/ር ፡ ለዓለም ፡ 'ላሊ' ፡ ጥላሁን ፡ ፫ኛውን ፡ አልበም ፡ በገበያ ፡ ላይ ፡ አውሏል ። ይህ ፡ የናርዶስ ፡ ሽቶዬ ፡ ተብሎ ፡ የተሰየመው ፡ አልበም ፡ ለቤተክርስቲያን ፡ የተሰጠ ፡ ነው ። አልበሙ ፡ በየቤትክርስቲያናት ፡ እየተሸጠ ፡ ነው ። ገዝተው ፡ ይገልገሉበት ፣ ቤተክርስቲያንንም ፡ ያግዙ !፲ ሐምሌ ፳ ፻ ፮ (July 17, 2014)Warning: Display title "መንፈሳዊ ፡ ዜና - Christian News" overrides earlier display title "መንፈሳዊ ፡ ዜና (Christian News)". __NOTITLE__