ጠብቀኝ (Tebeqegn) - ኬፋ ፡ ሚደቅሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኬፋ ፡ ሚደቅሳ
(Kefa Mideksa)

Kefa Mideksa 6.jpg


(6)

ሁሉም ፡ ይስማ
(Hulum Yesma)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2014)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 4:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኬፋ ፡ ሚደቅሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Kefa Mideksa)

ከሰማይ ፡ ሰማይ ፡ ወረደ
እንደ ፡ በግ ፡ ለእኔ ፡ ታረደ
ኢየሱስ ፡ ስለእኔ ፡ ታረደ
መች ፡ አንዲህ ፡ ቀላል ፡ ነው ፡ ነገሩ
የኢየሱስ ፡ የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩ (፪x)

አዝ፦ አበሳዬን ፡ ወሰደው ፡ ከላዬ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ በሃፍረት ፡ መታያዬ
ድፍረት ፡ ሆነኝ ፡ መግባት ፡ ወደ ፡ አባቱ
አስታረቀኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ
አማለደኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ (፪x)

የህማም ፡ ሰው ፡ ሆነ ፡ ደቀቀ
ኢየሱስ ፡ ስለእኔ ፡ ታመመ (፪x)
መራራውን ፡ ጽዋዬን ፡ ጠጣ
ሊያተርፈኝ ፡ ከሚመጣው ፡ ቁጣ
ሊያድነኝ ፡ ከሚመጣው ፡ ቁጣ

አዝ፦ አበሳዬን ፡ ወሰደው ፡ ከላዬ
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ በሃፍረት ፡ መታያዬ
ድፍረት ፡ ሆነኝ ፡ መግባት ፡ ወደ ፡ አባቱ
አስታረቀኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ
አማለደኝ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ (፪x)

ይቅር ፡ በላቸው ፡ አባ ፡ ማራቸው
ይህን ፡ ሁሉ ፡ ግፍ ፡ አትይባቸው
ብለህ ፡ ማልደሃል ፡ በዛ ፡ ፈተናህ
የሚያደርጉትን ፡ አያውቁምና

ከሙታን ፡ በኩር ፡ ነህ
ሞትን ፡ ድል ፡ የነሳህ
በአባትህ ፡ ቀኝ ፡ አለህ
የይሁድ ፡ አምበሳ (፪x)