ጐልጐታ ፡ ትመስክር (Golgota Timeskir) - ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ጐልጐታ ፡ ትመስክር ፡ ቀራንዮ ፡ ትናገር
የጌታ ፡ ኃይል ፡ ጣሩን ፡ የአኳሃኑን ፡ ነገር

አዝ፦ ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም

ነፍሱን ፡ ስለእኔ ፡ የሚያሰጥ ፡ መውደድ
መስቀል ፡ አሸክሞ ፡ አስጐንብሶ ፡ የሚያስኬድ
የጌታዬን ፡ ፍቅር ፡ ምን ፡ ይመጥነዋል
ከምንም ፡ ከምንም ፡ ከምንም ፡ ይበልጣል

አዝ፦ ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም

እንዴት ፡ እንዲወደኝ ፡ እኔ ፡ የማውቀው
የተወጋ ፡ ጐኑን ፡ እሱን ፡ ሳየው ፡ ነው
የእሾህ ፡ አክሊል ፡ አርጐ ፡ አንገቱን ፡ የደፋው
እኔን ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ ስቄ ፡ እንድኖር ፡ ነው

አዝ፦ ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም

ደም ፡ ግባት ፡ ውበትን ፡ የሌለው ፡ ተባለ
ስለበደሌ ፡ ሲል ፡ ደቀቀ ፡ ቆሰለ
አፉን ፡ አልከፈተም ፡ አምላኬ ፡ ዝም ፡ አለ
ሕመሜን ፡ ታመመ ፡ ደዌን ፡ ተቀበለ

አዝ፦ ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም

ሀዘኔን ፡ ምሬቴን ፡ በሰፍነጉ ፡ ሞልቶ
ኢየሱሴ ፡ ጠጣልኝ ፡ ከሰማያት ፡ መጥቶ
ሁሉን ፡ ጨርሶታል ፡ ምንም ፡ አላስቀረም
ለኔ ፡ ያስተረፈው ፡ ኾምጣጤኮ ፡ የለም

አዝ፦ ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከዚህስ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከአምላኬ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም
ከጌታ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም

ጐልጐታ ፡ ትመስክር ፡ ቀራንዮ ፡ ትናገር
የጌታ ፡ ኃይል ፡ ጣሩን ፡ የአኳሃኑን ፡ ነገር