From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ፋሬስ ፡ መዘምራን (Fares Choir)
|
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፮ (2014)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:37
|
ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች (Other Singles)
|
|
ሌሎች ፡ የፋሬስ ፡ መዘምራን ፡ አልበሞች (Other Albums ፡ by Fares Choir)
|
|
ለእኔ ፡ ነበር ፡ ያኔ ፡ መንገላታትህ
በግርፍና ፡ በጦር ፡ መቁሰልህ
መስቀል ፡ ተሸክመህ ፡ መውጣትህ
ሚስማር ፡ ተቸንክሮብህ ፡ መሞትህ
ለእኔ ፡ ነበር ፡ ያ ፡ ሁሉ ፡ መንገላታትህ
በሰዎች ፡ ፊት ፡ ተዋርደህም ፡ መሞትህ
ሃሌሉ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
ምን ፡ አይነት ፡ ክብር ፡ ምን ፡ አይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው
ያለህ ፡ ከኤደን ፡ ምድር ፡ ለወጣነው
አመጣጥ ፡ አሰራርህ ፡ ልዩ ፡ ነው
ላመስግንህ ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ
ምን ፡ አይነት ፡ ክብር ፡ ምን ፡ አይነቱ ፡ ፍቅር ፡ ነው
ለእኔ ፡ በኃጢአት ፡ . (1) .
ሃሌሉ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
ከሰማዩ ፡ ከክብር ፡ ዙፋንህ
ልታስታርቀን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ከአባትህ
ከማንም ፡ በላይ ፡ ገነህ ፡ ለከበርከው
ከዚያ ፡ ወርደህ ፡ ለእኛ ፡ ቤዛ ፡ የሆንከው
ግን ፡ አልቀረህም ፡ አልከለከለህ ፡ መቃብር
ተነሳህ ፡ ድል ፡ አድርገህ ፡ ለሞት ፡ ሳትበገር ፡ (ሳትበገር)
ሃሌሉ ፡ ሃሌሉያ (፰x)
|