ዘምር ፡ አለኝ (Zemer Alegn) - ኤፍሬም ፡ ዓለሙ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ኤፍሬም ፡ ዓለሙ
(Ephrem Alemu)

Ephrem Alemu 3.png


(3)

አቻ ፡ የሌለው
(Acha Yelielew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2010)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የኤፍሬም ፡ ዓለሙ ፡ አልበሞች
(Albums by Ephrem Alemu)

ጠላት ፡ የጻፈው ፡ የሞት ፡ ደብዳቤ
ተቀዶ ፡ ሳየው ፡ ደስ ፡ አለው ፡ ልቤ (ደስ ፡ አለው ፡ ልቤ)
ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ
ልቤም ፡ በደስታ ፡ ዘምር ፡ አለኝ (ዘምር ፡ አለኝ)

አዝ፦ ዘምር (፪x) (ዘምር ፡ አለኝ)
አምልክ (፪x) (አምልክ ፡ አለኝ)
ስገድ (፪x) (ስገድ ፡ አለኝ)
ለእርሱ ፡ ዘምር (ዘምር ፡ አለኝ)

ሸንጐ ፡ ሰብስቦብኝ ፡ መክሮብኛል ፡ ዝቶብኛል
ሰበብ ፡ ፈልጐብኝ ፡ ይዋጋኛል ፡ ይዞረኛል
የሚጠብቀኝ ፡ ስለማይተኛ ፡ እኔም ፡ አርፌ ፡ እስቲ ፡ ልተኛ
ዙሪያዬ ፡ ቢዞር ፡ ቢሽከረከረ ፡ እኔ ፡ እንደሆነ ፡ አለኝ ፡ ክብር
የተቀባ ፡ ሰው ፡ ሰልፉ ፡ ብዙ ፡ ነው
ነገር ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው

አዝ፦ ዘምር (፪x) (ዘምር ፡ አለኝ)
አምልክ (፪x) (አምልክ ፡ አለኝ)
ስገድ (፪x) (ስገድ ፡ አለኝ)
ለእርሱ ፡ ዘምር (ዘምር ፡ አለኝ)

የሲኦል ፡ በር ፡ ሲዘጋ ፡ ለእኔ ፡ ሌቱ ፡ ሲነጋ (ሲነጋ) ፡ ሲነጋ (ሲነጋ)
ጠላቴ ፡ ሲመሽበት ፡ ለማጁ ፡ ሰው ፡ በራለት ፡ ነጋለት (ነጋለት) ፡ በራለት (በራለት)
ደሙ ፡ ነው ፡ ምልክቴ ፡ አይገባም ፡ ሞት ፡ እቤቴ ፤ ከቤቴ (ከቤቴ) ፡ እቤቴ (ከቤቴ)
ያሳረገኝ ፡ ደሙ ፡ ነው ፡ ስለዚህ ፡ እዘምራለሁኝ ፡ ለጌታ (ለጌታ) ፡ በደስታ (በደስታ)

ምልክት ፡ አለብኝ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ በግምባሬ
ይፈራኛል ፡ ጠላት ፡ ከቶ ፡ አይቀርብም ፡ በሰፈሬ
በአጠገቤ ፡ ሺ ፡ በቀኝ ፡ አስር ፡ ሺ ፡ እየጣለልኝ ፡ ሆንኩኝ ፡ ድል ፡ ነሺ
ዙሪያዬ ፡ ስሜ ፡ በደሙ ፡ ታጥሯል ፡ ቅዱስ ፡ መንፈሱ ፡ ይጠብቀኛል
በድል ፡ ወጥቼ ፡ በድል ፡ እገባለሁ ፡ የእኔ ፡ ከለላ ፡ የእሳት ፡ ቅጥር ፡ ነው

ጠላት ፡ የጻፈው ፡ የሞት ፡ ደብዳቤ
ተቀዶ ፡ ሳየው ፡ ደስ ፡ አለው ፡ ልቤ (ደስ ፡ አለው ፡ ልቤ)
ጠላቴን ፡ ጥሎ ፡ ስላሳየኝ
ልቤም ፡ በደስታ ፡ ዘምር ፡ አለኝ (ዘምር ፡ አለኝ)

አዝ፦ ዘምር (፪x) (ዘምር ፡ አለኝ)
አምልክ (፪x) (አምልክ ፡ አለኝ)
ስገድ (፪x) (ስገድ ፡ አለኝ)
ለእርሱ ፡ ዘምር (ዘምር ፡ አለኝ)

ምህረቱ ፡ በዝቶብኝ ፡ በሕይወቴ ፡ አለሁኝ
የእኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ የሌለኝ
በቃ ፡ ማርኮኛል ፡ ተማርኬያለሁ ፡ ለፍቅሩ ፡ ብዛት ፡ እጄን ፡ ሰጥቻለሁ
ከአሁን ፡ በኋላ ፡ የምኖረው ፡ ለጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ልስሙ ፡ ነው
ዕድሜ ፡ ቀጥሎ ፡ ኑር ፡ ስላለኝ ፡ እኔም ፡ ለስሙ ፡ እኖራለሁኝ

ኦሮምኛ (ኦሮምኛውን ፡ ግጥም ፡ ይጻፉልን)