From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ።
|
አዝ፦ የዛሬው ቀኑ ደስ ይላል
ልናመሰግን መጥተናል
ከጠላት እጅ ያዳነንን
ቸሩ ጌታችን ይመስገን (፫x)
ደጉ ጌታችን ይመስገን (፪x)
ካሉን ያላወቁ ምን ሰበሰባቻው
ዕጣ እንደ ወጣለት ልክ የለው ደስታቻው ካሉን(፪)
በማጉረምረም ዘመን የሚሉት ምስጋና
እንዲህ የሚያስዘምር ምንስ ተገኘና
ካሉን(፪x)
ኧረ ወቶልን ነው የፅድቅ ፀሐይ
የመዳንን መንገድ በኢያሱስ ልናይ (፪x)
አንዳንዶች ነበርን ጠጪ የስካር ሰዎች
ብሎም የአመፅና የአጋንንት እስረኞች
አዎ(2x)
ልዩ ልዩ ቀንበር ነበር በጫንቃችን
ከእኛ ላይ ሰበረው ደርሶልን ጌታችን
አዎ አዎ
ከምህረቱ ማዕድ ቆርሶ ሰጠንና
እንዲህ ሰበሰበን እንድንል ምስጋና (፪)
ራሱን የሰጠን ያዳነን በመስቀል ለይ ሞቶ
ከዓለም እስክንመጣ ታገሰን ይህቺን ቀን አይቶ
ጌታ ባይደርስልን ይሄኔ ነበርን በጨለማ
ምህረት ላበዛልን አምጡ እንጂ ለክብሩ ምስጋና
አዝ፦ የዛሬው ቀኑ ደስ ይላል
ልናመሰግን መጥተናል
ከጠላት እጅ ያዳነንን
ቸሩ ጌታችን ይመስገን (፫x)
ደጉ ጌታችን ይመስገን (፪x)
ካሉን ያላወቁ ምን ሰባሰሳባቻው
ዕጣ እንደ ወጣለት ልክ የለው ደስታቻው(፪x)
ካሉን(፪x)
በማጉረምረም ዘመን የሚሉት ምስጋና
እንዲህ የሚያስዘምር ምንስ ተገኘና
ካሉን(፪x)
ኧረ ወጥቶልን ነው የፅድቅ ፀሐይ
የመዳንን መንገድ በኢየሱስ ልናይ (፪x)
|