የማያቋርጥ ፡ ምሥጋና (Yemayaquaret Mesgana) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 5.jpg


(5)

ዘላለማዊ
(Zelalemawi)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 4:06
ጸሐፊ (Writer): ዮአኪን ፡ ብርሃኑ
(Yoakin Berhanu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

የማያቋርጥ ፡ ምስጋና ፡ የማያቋርጥ ፡ ዝማሬ
     ይኸዉ ፡ መጣሁኝ ፡ ጨምሬ [፬X]

    ምስጋና ፡ ለጌታ [፪X]
    እልልታ ፡ ለጌታ [፪X]

ያጓራ ፡ ጠላት ፡ ያብዛ ፡ ቀረርቶ
ከሰራዉ ፡ ወጥመድ ፡ ማምለጤን ፡ አይቶ
ከቶ ፡ አላቆምም ፡ ማመስገን ፡ ማምለክ
ላዳነኝ ፡ ጌታ ፡ ፊቱ ፡ መንበርከክ

ሌባዉ ፡ ቀርቶታል ፡ በከንቱ ፡ ዛቻ
ከሩቅ ፡ እያየ ፡ መናደድ ፡ ብቻ [፬X]

    የማያቋርጥ ፡ ምስጋና ፡ የማያቋርጥ ፡ ዝማሬ
     ይኸዉ ፡ መጣሁኝ ፡ ጨምሬ [፬X]

    ምስጋና ፡ ለጌታ [፪X]
    እልልታ ፡ ለጌታ [፪X]

ፍጡር ፡ ፈርቼ ፡ የፈጣሪዬን ፡ ምስጋና ፡ አላቋርጥም
ለአሁኑ ፡ ዓለም ፡ ጓግቼ ፡ ዕንቁዬን ፡ ለአፈር ፡ አልሰጥም
በጥቂቱ ፡ ሆነ ፡ በብዙ ፡ የሚያድነዉን ፡ ታምኜ
ልበል ፡ ምስጋና ፡ አምልኮ ፡ የማያቋርጥ ፡ ዝማሬ [፫X]

ታላቁንና ፡ የተፈራዉን
የፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ የሆነዉን
አድርጌያለሁኝ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ጌታ
አልደነግጥም ፡ በሌላዉ ፡ ላፍታ
ለእርሱ ፡ ኖራለዉ ፡ ለእርሱ ፡ ሞታለዉ
ሥሙ ፡ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነዉ [፬X]

    የማያቋርጥ ፡ ምስጋና ፡ የማያቋርጥ ፡ ዝማሬ
     ይኸዉ ፡ መጣሁኝ ፡ ጨምሬ [፬X]

    ምስጋና ፡ ለጌታ [፪X]
    እልልታ ፡ ለጌታ [፪X]