ነፍሴ ፡ ተስፋ (Nefse Tesfa) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 5.jpg


(5)

ዘላለማዊ
(Zelalemawi)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:08
ጸሐፊ (Writer): ዮአኪን ፡ ብርሃኑ
(Yoakin Berhanu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ነፍሴ ፡ ተስፋ ፡ እያደረገችህ
    ምትዉልብህ ፡ ምታድርብህ
    ህያዉ ፡ ተስፋዬ
    ልቤ ፡ አንተን ፡ አምኖ ፡ ልቤ
    ልቤ ፡ ባንተ ፡ ፀና ፡ ልቤ
[፪X]

ጓዳዬን ፡ ሙላ ፡ አደባባዬን
ልኑር ፡ አንተን ፡ ስል ፡ ቀሪ ፡ ዘመኔን
ምንም ፡ አልሆንም ፡ አንተን ፡ ብያለሁ
የደህንነቴን ፡ እራስ ፡ ይዣለሁ

ልቤ ፡ ፀናልኝ ፡ አንተን ፡ በማመን
ፍጹም ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የለብህ ፡ እንከን
ነፍሴ ፡ ትላለች ፡ ህያዉ ፡ ተስፋዬ
ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ መሸሸጊያዬ

    ነፍሴ ፡ ተስፋ ፡ እያደረገችህ
    ምትዉልብህ ፡ ምታድርብህ
    ህያዉ ፡ ተስፋዬ
    ልቤ ፡ አንተን ፡ አምኖ ፡ ልቤ
    ልቤ ፡ ባንተ ፡ ፀና ፡ ልቤ
[፪X]

አንተን ፡ ያደረገ ፡ መድህን ፡ አንተን ፡ ያደረገ ፡ ጥላ
ሆነህለት ፡ አየሁ ፡ እንጂ ፡ ክፉ ፡ እንዳይነካዉ ፡ ከለላ

እኔስ ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ካሉት ፡ ከለላ ፡ ካሉት ፡ አጥር
[እንደምትበልጥ ፡ አይቻለዉ ፡ እግዚአብሔር
] [፪X]