ክብር ፡ ሁሉ (Keber Hulu) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 5.jpg


(5)

ዘላለማዊ
(Zelalemawi)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2018)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 6:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

እንኳን ፡ ልመካ ፡ እንዲህ ፡ ነኝ ፡ ብዬ
 እኔ ፡ እኔ ፡ ልል ፡ ቃል ፡ አስረዝሜ
'እ'ን ፡ አስጀምሮ ፡ 'ኔ'ን ፡ የሚያስጨርሰኝ
 ከራሴ ፡ ምለው ፡ አንዳችም ፡ የለኝ

አሁን ፡ የሆንኩትን ፡ መሆን ፡ የመቻሌ
ጌታ ፡ በአንተ ፡ እኮነው ፡ አይደለም ፡ በእኔ

ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተይሁን x ፬

እኔ ፡ ለማለት ፡ ፓ እንዲሉልኝ ፡ ፡ ሰዎች ፡ ብጠራ ፡
ማንም ፡ አይገኝ ፡ በአሸዋ ፡ ላይ ፡ ቤቴን ፡ ስሥራ ፡
እርሱ ፡ ነው ፡ ስል ፡ ግን ፡ ተሰብሰቡና ፡ "አዎ" ፡ በሉልኝ
 ይህን ፡ ላረገው ፡ ታማኙ ፡ ጌታ ፡ (ክብር ፡ አምጡልኝ) ፡ x ፰

ስሙኝ ፡ ወገኖች ፡ ይህን ፡ ስናገር ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፡ ለሆነው ፡ ነገር
እንኳን ፡ ልታበይ ፡ እኔን ፡ ላበዛ ፡ ትንፋሽ ፡ መንገዱን ፡ ከፍሎ ፡ እንደገዛ
ከቶ ፡ አልመካም ፡ እንዲያው ፡ በከንቱ ፡ ከእኔ ፡ ሳይሆን ፡ ሁሉ ፡ ነው ፡ በእርሱ
እ ፡ የሚለውን ፡ ፊደል ፡ ጀምሬ ፡ 'ኔ'ን ፡ ለመጨረስ ፡ ኃይል ፡ የለኝ ፡ እኔ

እያልኩኝ ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ጌታ
ሁሉን ፡ አድርገህ ፡ የምታስመካኝ ፡ ሆንከኝ ፡ አለኝታ

ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተይሁን x ፬

ኧረ ፡ ምንድነው ፡ ከእኔ ፡ ነው ፡ የምለው
ኃይሌ ፡ ብርታቴ ፡ እጄ ፡ ያረገው
ማበዛላቸው ፡ ብዙ ፡ እኔዎች
ሆኑ ፡ ምላቸው ፡ በእኔ ፡ ክንዶች
ምንም ፡ የለኝም ፡ የሚያስብለኝ ፡ እኔ
ክብር ፡ ሚገባው ፡ ለአንተ ፡ ጌታዬ

እንኳን ፡ ልመካ ፡ እንዲህ ፡ ነኝ ፡ ብዬ
እኔ ፡ እኔ ፡ ልል ፡ ቃል ፡ አስረዝሜ
'እ'ን ፡ አስጀምሮ ፡ 'ኔ'ን ሚያስጨርሰኝ
ከራሴ ፡ ምለው ፡ አንዳችም ፡ የለም

ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተይሁን # ፬