From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ።
|
|
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ (Endale Woldegiorgis)
|
|
፭ (5)
|
ዘላለማዊ (Zelalemawi)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፲ (2018)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፫ (13)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:26
|
ጸሐፊ (Writer):
|
ዮአኪን ፡ ብርሃኑ (Yoakin BerhanuProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች (Albums by Endale Woldegiorgis)
|
|
አቤቱ ፡ ለቀዳሚነትህ ፡ ጥንት
ለኋላኛናትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለህ [፪x]
አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ [፬X]
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ [፬X]
ጌታ ፡ ዘመናትህ ፡ ዓማታትህ ፡ ቢቆጠሩ ፡ አያልቁም
ለአንተ ፡ ምን ፡ ቢበዙ ፡ የዕድሜ ፡ ገደብ ፡ ከቶ ፡ አይችሉም ፡ ሊሰጡህ
ዘመናትን ፡ አሳልፈህ ፡ አሳልፈህ
አንተ ፡ ብቻ ፡ ትኖራለህ ፡ ትኖራለህ
ዘላለማዊ ፡ ነህ
ዘላለማዊ ፡ ነህ [፬X]
አናልፍም ፡ ያሉ ፡ አለፉ
አንሞትም ፡ ያሉትም ፡ ሞቱ
ኃያላን ፡ ለአንተ ፡ ሰገዱ
ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ አሉ
የአንተ፡ አልፋ ፡ የአንተ ፡ ኦሜጋ
ሁሌ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ መሽቶ ፡ ሲነጋ
መንግስትህ ፡ ቋሚ ፡ ዘላለማዊ
ሁሉ ፡ ሲያከትም ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ነዋሪ
ዘላለማዊ ፡ ነህ
ዘላለማዊ ፡ ነህ [፬X]
ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ
አንተ ፡ ያልነበርክበት ፡ ጊዜ
ለቅጽበት ፡ አልነበረም ፡ አይኖርም
ስልጣንህ ፡ መንግስትህ ፡ ነው ፡ ከዘላለም [፬x]
|