From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ (እህህ) ፡ ወደፊት (እህህ) ፡ እገሰግሳለሁ
የኋላዬን ፡ ትቼ ፡ የፊቴን ፡ እይዛለሁ (፪x)
እይዛለሁ (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው
እይዛለሁ (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው
1/ለነሰንበላጥ ፡ ለነጊሳም
ና ውረድ ፡ ለሚል ፡ ሥራ ፡ ሊያስቆም
ከንቱ ፡ ለሆነው ፡ ለዚህ ፡ ቃላቸው
አልንበረከክ ፡ ከቶ ፡ አልሰማቸው (፪x)
2/ለሥጋ ፡ ጥቅም ፡ ለነፍሴ ፡ ክሳት
እኔ ፡ አልለምንም ፡ በዚህስ ፡ ወራት
ለአምላኬ ፡ ደስታ ፡ እሆንለታለሁ
ብዙ ፡ ሥራ ፡ ነው ፡ ከፊቴ ፡ ያለው (፪x)
አዝማች:> ዝምብዬ (እህህ) ፡ ወደፊት (እህህ) ፡ እገሰግሳለሁ
የኋላዬን ፡ ትቼ ፡ የፊቴን ፡ እይዛለሁ (፪x)
እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው
እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው
3/ለይናቅ ፡ ልጆች ፡ ለነፊልሞች
በዐይን ፡ ሲታዪ ፡ ለረዣዥሞች
ወዬው ፡ እዬዬ ፡ ብዬ ፡ አልጮህም
እኔ ፡ የማመልከው ፡ ሽንፈት ፡ አያውቅም (፪x)
4/ድንቃ ፡ ድንቅ ፡ አድርጐ ፡ አንዴ ፡ ጠርቶኛል
የእውነትን ፡ መንገድ ፡ አሳይቶኛል: ቀብሬ ልምጣ ብዬ አልጠይቅም
ፍሬ ፡ ለሌለው ፡ ጊዜዬን ፡ አልፈጅም (፪x)
አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ (እህህ) ፡ ወደፊት (እህህ) ፡ እገሰግሳለሁ
የኋላዬን ፡ ትቼ ፡ የፊቴን ፡ እይዛለሁ (፪x)
እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው
እይዛለሁ (እይዛለሁ) (፪x) ፡ ለጦር ፡ ያስከተተኝ ፡ እርሱን ፡ ደስ ፡ ያሰኘው
|