From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አርበኛ ፡ ነኝ (፪x) ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ
ጌታም ፡ አድርጐኛል ፡ የእውነት ፡ ሰራተኛ (፪x)
አልፈራ ፡ አልደነግጥ ፡ ልቤም ፡ አይሸበር
ጌታ ፡ ፍርሃቴን ፡ አድርጐታል ፡ ሰበር (አድርጐታል ፡ ሰበር)
ጉልበታም ፡ መንፈሱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ተለቋል
ጠላቴ ፡ ይህን ፡ አይቶ ፡ ሁሌ ፡ ያንዣብባል
ይዙር ፡ ያንዣብ ፡ እንጂ ፡ ምኔን ፡ ያገኘዋል
(ይዙር ፡ ያንዣብ ፡ እንጂ ፡ ምኔን ፡ ያገኘዋል)
እኔን ፡ ሊነካ ፡ ሲል ፡ እሳት ፡ ይቀድመዋል (፪x)
አዝ፦ አርበኛ ፡ ነኝ (፪x) ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ
ጌታም ፡ አድርጐኛል ፡ የእውነት ፡ ሰራተኛ (፪x)
ቅጥሬ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ጦር ፡ ደሞዜ ፡ በሰማይ
ይሄ ፡ ስለሆነ ፡ ምንም ፡ ምንም ፡ አላይ (ምንም ፡ ምንም ፡ አላይ)
በሃይል ፡ ተሞልቼ ፡ በብርቱ ፡ እዋጋለሁ
ያዘዘኝን ፡ ጌታ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ላሰኘው
አዝ፦ አርበኛ ፡ ነኝ (፪x) ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ
ጌታም ፡ አድርጐኛል ፡ የእውነት ፡ ሰራተኛ (፪x)
በጠቅላዩ ፡ ገዤ ፡ በኢየሱስ ፡ ታዝዤ
ወደጠላት ፡ መንደር ፡ በመንፈስ ፡ ገስግሼ (በመንፈስ ፡ ገስግሼ)
ጉድ ፡ ሳልሰራ ፡ አልመጣም ፡ በፍፁም ፡ በባዶ
አየዋለሁ ፡ ጠላት ፡ በእሳት ፡ ቆስሎ ፡ ነዶ
ይዙር ፡ ያንዣብ ፡ እንጂ ፡ ምኔን ፡ ያገኘዋል
(ይዙር ፡ ያንዣብ ፡ እንጂ ፡ ምኔን ፡ ያገኘዋል)
እኔን ፡ ሊነካ ፡ ሲል ፡ እሳት ፡ ይቀድመዋል (፪x)
ደግሞ ፡ ለጠላቴ ፡ እድል ፡ ፈንታ ፡ አልሰጥም
ከደሊላ ፡ ጭን ፡ ላይ ፡ ተኝቼ ፡ አልገኝም (አልገኝም)
የጌታዬ ፡ መንፈስ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ስላለ
እንደወደደው ፡ ያድርገኝ ፡ እርሱ ፡ እንደፈለገ
አዝ፦ አርበኛ ፡ ነኝ (፪x) ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ
ጌታም ፡ አድርጐኛል ፡ የእውነት ፡ ሰራተኛ (፪x)
|