Endale Woldegiorgis/Yewengiel Arbegna/Yemedan Qendie

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

====

የመዳን ፡ ቀንዴ ፡ ጌታዬ
አምላኬ ፡ ያስነሳው ፡ ለእኔ
ከአብ ፡ ጋር ፡ ያስተራረቀኝ
ዘወትር ፡ ሚማልድልኝ
ውዴ ፡ የመዳን ፡ ቀንዴ(፬x)


እነርሱ ፡ እንዳይኖሩ ፡ ሞት ፡ ከልክሏቸዉ

ካህናት ፡ የሆኑት ፡ ብዙዎች ፡ ናቸው

እርሱ ፡ ግን ፡ ዘለዓለም ፡ ሚኖር ፡ ስለሆነ

ዘወትር ፡ ይኖራል ፡ ለእኔ ፡ እየማለደ


የመዳን ፡ ቀንዴ ፡ ጌታዬ
አምላኬ ፡ ያስነሳው ፡ ለእኔ
ከአብ ፡ ጋር ፡ ያስተራረቀኝ
ዘወትር ፡ ሚማልድልኝ
ውዴ ፡ የመዳን ፡ ቀንዴ(፬x)


በሚያገለግሉት ፡ በነቢያቱ ፡ አፍ

የተነገረለት ፡ በዘመናት ፡ ምዕራፍ

እንደተባለለት ፡ ድንገት ፡ ከተፍ ፡ አለ

እግዚአብሔር ፡ ለአብራሃም ፡ በቃሉ ፡ እንደማለ


አማላጄ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው ፡ ወዳጄ (፪x)


የጥሉን ፡ ግድግዳ ፡ ላያዳግም ፡ አንዴ

አፈራርሶ ፡ ጣለው ፡ ይህ ፡ የመዳን ፡ ቀንዴ

ለእኔ ፡ ሆኖልኛል ፡ ታዳጊና ፡ ቤዛ

በእውነት ፡ ኢየሱሴ ፡ ሃያል ፡ ነው ፡ ሲበዛ


የመዳን ፡ ቀንዴ ፡ ጌታዬ
አምላኬ ፡ ያስነሳው ፡ ለእኔ
ከአብ ፡ ጋር ፡ ያስተራረቀኝ
ዘወትር ፡ ሚማልድልኝ
ውዴ ፡ የመዳን ፡ ቀንዴ(፬x)


ይገርማል ፡ ሲነሳ ፡ ማንም ፡ አልጠበቀው

ደም ፡ ግባት ፡ የሌለው ፡ ነበር ፡ የህማም ፡ ሰው

ድንገት ፡ ጥሶ ፡ ሄዶ ፡ እኔንም ፡ አስጣሰኝ

ጠላትን ፡ ልመታው ፡ አሳልፎ ፡ ሰጠኝ


ሊቀ-ካህን ፡ ሆኖልኛል ፡ ሊቀ-ካህን (፪x) (አማላጄ)

አማላጄ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው ፡ ወዳጄ (፪x)

ሊቀ-ካህን ፡ ሆኖልኛል ፡ ሊቀ-ካህን (፪x)

አማላጄ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው ፡ ወዳጄ (፪x) Big text ====