ቅድስና (Qedesena) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 1.jpg


(1)

የወንጌል ፡ አርበኛ
(Yewengiel Arbegna)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 5:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ሰው ፡ ሳይል ፡ ቀደስ ፡ በዓይኖቼ ፡ አማትሬ
እግዚአብሔር ፡ ያውቃል ፡ የድብቅ ፡ ነገሬን
እኔ ፡ ግን ፡ ከቃሉ ፡ አወቅሁ ፡ አንድ ፡ ነገር

አዝ፦ ቅድስና ፡ አሃሃ ፡ እግዚአብሔር
መቀደሴ ፡ ኤሄሄ ፡ ኢየሱሴ

ጉዳና ፡ አይደል ፡ ኑሮ ፡ ይሁን ፡ ከዚያ ፡ ጀርባ
የእልፍኝ ፡ ነገሬን ፡ የሚያይ ፡ አለና
እንዲህ ፡ ከሆነ ፡ ኑሮ ፡ ይቅር ፡ ለዘለዓለም
አልተጠራሁኝም ፡ ልመስል ፡ ይህን ፡ ዓለም

አዝ፦ ቅድስና ፡ አሃሃ ፡ እግዚአብሔር
መቀደሴ ፡ ኤሄሄ ፡ ኢየሱሴ (፪x)

አባቴን/ኢየሱስ ፡ እንዲህ ፡ ስል ፡ እለምንሃለሁ
ፍለጋን ፡ መሻቴን ፡ ይህን ፡ አድርጌያለሁ
(፪x)
ከብረህ (፫x) ፡ ታይ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ
ነግሠህ (፫x) ፡ ታይ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እስኪያይ

ማነው ፡ እራሱን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ የሚቀድስ
ስለ ፡ አምላኩ ፡ ኖሮ ፡ ጌታውን ፡ የሚያስደስት (፪x)
እርሱ ፡ ብሩክ ፡ ነዉ ፡ ዘመኑም ፡ የተድላ
የድካሙን ፡ ፍሬ ፡ ቁጭ ፡ ብሎ ፡ የሚበላ

ሰው ፡ ሳይል ፡ ቀደስ ፡ በዓይኖቼ ፡ አማትሬ
እግዚአብሔር ፡ ያውቃል ፡ የድብቅ ፡ ነገሬን
እኔ ፡ ግን ፡ ከቃሉ ፡ አወቅሁ ፡ አንድ ፡ ነገር

አዝ፦ ቅድስና ፡ አሃሃ ፡ እግዚአብሔር
መቀደሴ ፡ ኤሄሄ ፡ ኢየሱሴ (፪x)

ከብረህ (፫x) ፡ ታይ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ
ነግሠህ (፫x) ፡ ታይ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እስኪያይ