ማን ፡ ጠገበ (Man Tegebe) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 1.jpg


(1)

የወንጌል ፡ አርበኛ
(Yewengiel Arbegna)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:44
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ማን ፡ ጠገበ (ዬ) ፡ ማን ፡ ረካ
ቃላት ፡ ቢደረደር ፡ በዝማሬ ፡ ተርታ
እኔ ፡ በበኩሌ ፡ አልረካሁም
አንተን ፡ የሚገልጥ ፡ ቃል ፡ አላገኘሁም
እንዲያውም ፡ ለክብርህ ፡ ባሉኝ ፡ ቃላቶቼ
ላደናንቅህ ፡ እንጂ ፡ መቅደስህ ፡ ገብቼ
(፪x)

እንካ ፡ ጌታ ፡ ጣፋጭ ፡ ምሥጋናዬን
ስለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ልግለጽ ፡ በዜማዬ (፪x)

ቃልህን ፡ ልከኸው ፡ በሕይወቴ ፡ ድንቅን ፡ ሰራ
ከፊቴ ፡ ተነሳ ፡ የገዘፈው ፡ ያ ፡ ተራራ
ታዲያ ፡ ለማመስገን ፡ ማን ፡ ከልክሎኝ ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ከልካይ ፡ የለብኝም ፡ ተፈትቼ ፡ አመልካለሁ (፪x)

ሌላ (፬x) ፡ እንደአንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ሌላ (፪x)

የሚጤሰውን ፡ ጧፍ ፡ ሳታጠፋ ፡ ቅጥቅጡን ፡ ሸምበቆ ፡ ሳትሰብረው (፪x)
ድምጽን ፡ ሳታሰማ ፡ ትመጣለህ ፡ ፍጥረትን ፡ መገረም ፡ ትሞላለህ (፪x)

ልግባ ፡ ወደአንተ ፡ በአምልኮ
በዐይኔ ፡ አሳይቶኛል ፡ ክንድህ ፡ ድንቅ ፡ ሰርቶ
ተቀበለኝ ፡ ምሥጋናዬን
ውዴ ፡ ለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ይህን ፡ ስጦታዬን
የአባቶች ፡ አምላክ ፡ ዘምርልሃለሁ
አፌን ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ልቤን ፡ እሰጥሃለሁ
(፪x)

የሚጤሰውን ፡ ጧፍ ፡ ሳታጠፋ ፣ ቅጥቅጡን ፡ ሸምበቆ ፡ ሳትሰብረው (፪x)
ድምጽን ፡ ሳታሰማ ፡ ትመጣለህ ፣ ፍጥረትን ፡ መገረም ፡ ትሞላለህ (፪x)

ማን ፡ ጠገበ (ዬ) ፡ ማን ፡ ረካ
ቃላት ፡ ቢደረደር ፡ በዝማሬ ፡ ተርታ
እኔ ፡ በበኩሌ ፡ አልረካሁም
አንተን ፡ የሚገልጥ ፡ ቃል ፡ አላገኘሁም
እንዲያውም ፡ ለክብርህ ፡ ባሉኝ ፡ ቃላቶቼ
ላደናንቅህ ፡ እንጂ ፡ መቅደስህ ፡ ገብቼ
(፪x)

ሌላ (፬x) ፡ እንደአንተ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ ሌላ (፫x)
ሌላ (፪x) ፡ ሌላ (፪x)