From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ
ልጁ ፡ አደረገኝ ፡ መንፈሱን ፡ ሰጥቶ ፡ ጌታ
ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ
አገልጋይ ፡ አደረገኝ ፡ በዘይት ፡ ቀብቶ ፡ ጌታ
የቅባቱ ፡ ውፍረት ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበረው (አሃሃ)
የተጫነኝንም ፡ ሸክብ ፡ አወረደው (ኦሆሆ)
እስራቴን ፡ ሁሉ ፡ የፈቱ ፡ እጆቹ
የምለው ፡ የለኝም ፡ በእውነት ፡ ይባረኩ (፪x)
የጐልያድን ፡ ቁመት ፡ የልብሱን ፡ ክብደት (አሃሃ)
አትኜ ፡ አይደለሁም ፡ የእርሱን ፡ የጦር ፡ ስልት (ኦሆሆ)
ምንም ፡ አይደንቀኝም ፡ ጦሩና ፡ ጡሩሩ
ወድቆ ፡ ይከሰከሳል ፡ በፊት ፡ በግንባሩ (፪x)
በእኔ ፡ ተማምኗል ፡ አስጥለዋለዉ
ስሜንም ፡ አውቋል ፡ ጋርደዋለሁ
አለና ፡ ጌታ ፡ በበቀል ፡ ወጥቶ
ጠላቴን ፡ ጣለው ፡ እራሱን ፡ መቶ
የረሳኸኝ ፡ መስሎት ፡ ጭፍራውን ፡ ሰብስቦ (አሃሃ)
ውድቀቴን ፡ እንዲያዩ ፡ ወዳጆቹን ፡ ጠርቶ (ኦሆሆ)
ጠአቱን ፡ ቀስሮ ፡ ጉድ ፡ እዩ ፡ ሲላቸው
እኔን ፡ አአሰብክና ፡ ሃፍረት ፡ አለበስከው ፡ እህ (፪x)
ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ
ልጁ ፡ አደረገኝ ፡ መንፈሱን ፡ ሰጥቶ ፡ ጌታ
ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ
አገልጋይ ፡ አደረገኝ ፡ በዘይት ፡ ቀብቶ ፡ ጌታ
ፈርጠም ፡ ወፈር ፡ ያለ ፡ እልያብ ፡ እያለ (አሃሃ)
በሰው ፡ የተናቀን ፡ ዳዊት ፡ ይቀብ ፡ ያለ (ኦሆሆ)
መረሳቴን ፡ ሽሮ ፡ በኢየሱስ/በልጁ ፡ ያሰበኝ
ምትክ ፡ የማይኖረው ፡ ለኔስ ፡ አምላክ ፡ አለኝ (፪x)
በእኔ ፡ ተማምኗል ፡ አስጥለዋለዉ
ስሜንም ፡ አውቋል ፡ ጋርደዋለሁ
አለና ፡ ጌታ ፡ በበቀል ፡ ወጥቶ
ጠላቴን ፡ ጣለው ፡ እራሱን ፡ መቶ (፪x)
|