አምላካችን (Amlakachen) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

Endale Woldegiorgis 1.jpg


(1)

የወንጌል ፡ አርበኛ
(Yewengiel Arbegna)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 4:48
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

አምላካችን ፡ መጠጊያችን ፡ ኃይላችን
ባገኘነው ፡ በታላቅ ፡ መከራ ፡ ረዳታችን (፪x)

ሆኖልናል (፪x)

የማዳን ፡ ደስታ ፡ ለእኛ ፡ ሰጥቶን
በሽታ ፡ መንፈስ ፡ ይኸው ለውጦ
ከዚም ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ ለማንም ፡ የለውም
ስለወዳጆቹ ፡ የሚሰጥ ፡ እራሱን
(፪x)

ሄደን ፡ ነበር ፡ ወደ ፡ ተራራ
አይተን ፡ ነበር ፡ በብዙ ፡ አቅጣጫ
ተስፋ ፡ ሚሆን ፡ ቢታጣም ፡ በዚያ
አግኝተናል ፡ የዓይን ፡ ማረፊያ
የዓይኖቻችን ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ
የዓይኖቻችን ፡ ማረፊያ ፡ ኢየሱስ

አምላካችን ፡ መጠጊያችን ፡ ኃይላችን
ባገኘነው ፡ በታላቅ ፡ መከራ ፡ ረዳታችን (፪x)

ሆኖልናል (፪x)

መች ፡ በቀላሉ ፡ ሚታለፍ ፡ ነበር
በሕይወታችን ፡ የሆነው ፡ ነገር
እርሱ/ጌታ ፡ ሲመጣልን ፡ ወጥመድ ፡ ተሰበረ
የተከሰስንበት ፡ እዳችን ፡ ተሻረ
(፪x)

ሄደን ፡ ነበር ፡ ወደ ፡ ተራራ
አይተን ፡ ነበር ፡ በብዙ ፡ አቅጣጫ
ተስፋ ፡ ሚሆን ፡ ቢታጣም ፡ በዚያ
አግኝተናል ፡ የዓይን ፡ ማረፊያ

የዓይኖቻችን ፡ ማረፊያ ፡ ጌታ
የዓይኖቻችን ፡ ማረፊያ ፡ ኢየሱስ (፫x)